Find Us

 

 
Likes

Latest Invitation for Bid Latest Invitation for Bid

Showing 1 - 3 of 78 results.
Items per Page 3
of 26

Latest Invitation for Bid Latest Invitation for Bid

Top News Top News

የዛሪማ-ማይፀብሪ 7ዐ ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡

የዛሪማ-ማይፀብሪ 7ዐ ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ሥራ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተጠናቆ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል አመራሮች የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት መመረቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አስታወቀ:: የዚህን ከሊማሊሞ ተራራማ እና ገደላማ መልክዓ ምድር ባሻገር ከዛሪማ ተነስቶ በቅርቡ ከተጠናቀቀው የሽሬ-ማይፀብሪ መንገድ ጋር የሚያስተሳስረውን የመንገድ ግንባታ ያከናወነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ሲሆን የምህንድስና የቁጥጥርና የማማከር ሥራውን በጋራ ያከናወኑት መታፈሪያና ልደት አማካሪ ድርጅቶች ናቸው፡፡ የመንገድ ኘሮጀክቱ ከ219 በላይ ለሚሆኑ ቋሚ እና ከ4000 በላይ ለሚሆኑ ጊዜያዊ ሰራተኞች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡
 

 

 

 

 


ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የ 3 መንገዶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመንገባት የሚያስችሉ የኮንትራት ስምምነቶች ተፈረሙ፡፡   

የሁለተኛው አምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አካል የሆኑትንና በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የሚገኘውን የቱርሚ -ኦሞ ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘውን የሮቤ-ጋሰራ ፣ በጋምቤላ - ኤሊያ ፣ የመንገድ ኘሮጀክቶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመገንባት የሚያስችሉ የኮንትራት ውል ስምምነቶች ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2009 ዓ.ም በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈረሙ፡፡ መንገዶቹ በአጠቃላይ 201.35 ኪ.ሜ ርዝመት የሚሸፍኑ ሲሆን፣ ለግንባታቸውም ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡ መንገዶቹ ከዚህ ቀደም ምንም የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበረባቸውና በጠጠር መንገድ ደረጃ የነበሩ ሲሆን ፣ ካላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንፃር ታይቶ በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ደረጃ እንዲገነቡ የውል ስምምነቱ ተፈርሟል፡፡ግንባታው በአገር በቀል ተቋራጮች የሚካሄድ ሲሆን የኘሮጀክቶቹ ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ነው፡፡

 


 

የትራንስፖርት ሚንስትር ድኤታ ክቡር አቶ አብዲሳ ያዴታ፣ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ግርማይ እና የባለስልጣኑ ኃላፊዎች የሞጆ - መቂ እና የመቂ - ዝዋይን የፍጥነት መንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

የትራንስፖርት ሚንስትር ድኤታ ክቡር አቶ አብዲሳ ያዴታ፣ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ግርማይ እና የባለስልጣኑ ኃላፊዎች የሞጆ -ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ክፍል የሆኑትን የሞጆ - መቂንና የመቂ - ዝዋይን የፍጥነት መንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም መጎብኘታቸውን የኢመባ ኮምንኬሽን ዳይሬክቶሬት ገለጸ፡፡ የሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ውስጥ የተካተተውና የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት አንድ ሞጆ-መቂ 56.4 ኪሜ እና የመቂ ዝዋይ 37 ኪ ሜ መንገድ በድምሩ 5.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግናባታቸው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

 


ከ7.9 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 7 የመንገድ ኘሮጀክቶችን ለመንገባትና ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ የኮንትራት ስምምነቶች ተፈረሙ፡፡

የሁለተኛው አምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አካል የሆኑትንና በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኘትን የዳዬ - ጪሪ - ናንሰቦ፣ የመነቤኛ-ፊንጫ-ሻምቡ -ባኮ  ኮንት 1 የመነቤኛ-ፊንጫ-ሻምቡ ፣ የጭኮ-ይርጋ ጨፌ፣ በሶማሌ ክልል የሚገኘውን የጂጂጋ -  ገለልሽ- ደገህመዶ-ሰገግ የመጀመሪያ ኮንትራት ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የሚገኙትንየሙካቱሪ - አለም ከተማየመጀመሪያ ኮንትራት የሆነውን ሙካቱሪ - ኮከብ መስክ፣ እንዲሁም በአማራ ክልል የሚገኘውን  የአለም ከተማ - ድጎሎእና የድጎሎ - ከለላየመንገድ ኘሮጀክቶችን በአስፋልት ደረጃ ለመገንባትና ለማሳደግ የሚያስችሉ የውል ስምምነቶች ዛሬ መጋቢት 4 ቀን 2009 ዓ.ም በ8፡3ዐ ላይ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈረሙ፡፡ መንገዶቹ በአጠቃላይ 468.8 ኪ.ሜ ርዝመት የሚሸፍኑ ሲሆን፣ ለግንባታቸውም ከ7.9 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያስፈልግ ታውቋል፡፡ መንገዶቹ ከዚህ ቀደም  ምንም የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበረባቸውና በጠጠር መንገድ ደረጃ የነበሩ ሲሆን ፣ ካላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንፃር ታይቶ በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ደረጃ እንዲገነቡ የውል ስምምነቱ ተፈርሟል፡፡  

 


የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት አንድ ሞጆ-መቂ 56.4 ኪሜ መንገድ አስፋልት ማንጠፍ ስራ ተጀመረ፡፡

የሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ውስጥ የተካተተውና የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት አንድ ሞጆ-መቂ 56.4 ኪሜ መንገድ አስፋልት ማንጠፍ ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡ የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት 1 የሞጆ - መቂ 56.4 ኪሜ መንገድ ግንባታ ለማካሄድ በ3,669,604,000 (በሶስት ቢሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሚሊዮን ስድስት መቶ አራት ሺህ) ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ቻይና ሬልዌይ ሰባተኛ ግሩፕ የተባለ የቻይና አለም አቀፍ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ነው፡፡ የዚህን መንገድ ግንባታ የማማከርና የቁጥጥር ስራ የሚያካሂዱት ኤልኢኤ ኢንትርናሽናል ሊሚትድ ካናዳ ፣ ኤልኢኤ አሶሴትስ ሳውዝ ኤሲያ ፕራይቬት ሊሚትድ(LASA) ከዩናይትድ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነር ፒኤልሲ (UNICONE) ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡

 


የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አነስተኛ ትራፊክ የሚያስተናግዱ የመንገዶች ዲዛይን የአሰራር ማኑዋልን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ውይይት አካሄደ፡፡ 

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ያስጠናው አነስተኛ ትራፊክ የሚያስተናግዱ የመንገዶች ዲዛይን የአሰራር ማኑዋል(Design Manual for Low volume Roads)ዝግጅት መጠናቀቁን መነሻ በማድረግ ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ውይይት ማካሄዱን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ግርማይ፣ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሃገር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች፣ የክልል የመንገድ ኤጀንሲዎች ተወካዮች፣የአገር በቀል የግል ሥራ ተsራጮች'የአማካሪ ድርጅቶች ፣ የዓለም ባንክ፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም  በሒልተን ሆቴል የውይይቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡  

 


 

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአራት መንገዶችን ደረጃ ለማሳደግና ለመገንባት የሚያስችሉ   የኮንትራት ስምምነቶች   ተፈረሙ፡፡

የሁለተኛው አምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አካል የሆኑት በጋምቤላ ክልል የሚገኘው ኮንትራት አንድ አቦቦ - 76 ኪሎ ሜትር የዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኘው የአሶሳ - ዳለቲ - ባሩዳ ኮንትራት አንድ 36 ኪሎ ሜትር መንገድ፣ በደቡብ ክልል የሚገኘው የሳይ-ማጂን 29 ኪ.ሜ እና በአማራ ክልል የሚገኘውን 4.9 ኪ.ሜ የደብረ ማርቆስ ከተማ መንገዶችን በአስፋልት ደረጃ ለመገንባት እና ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ የውል ስምምነቶች  ህዳር 28 ቀን 2009 ዓ.ም በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈረሙ፡፡

 


 

የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ-ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ኮንትራት አንድና ሁለት ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ውስጥ የተካተተውና የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው እና 202.48 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የሞጆ- ሐዋሳ ዘመናዊ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክት ኮንትራት አንድ ሞጆ-መቂና ኮንትራት ሁለት መቂ-ዝዋይ የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ ነዉ ፡፡

  


 

 

 

.