ከ 179.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባዉ የሳዉላ - ቃቆ (ኮንትራት 1) መንገድ ተመረቀ
የኢፌዴሪ መንግስት በሶስተኛዉ የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ከሚያስገነባቸዉና ከሚያሻሽላቸዉ መንገዶች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ እና በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የሚገኘዉ የሳዉላ - ቃቆ (ኮንትራት 1) ፕሮጀክት ደረጃዉን በጠበቀ የጠጠር መንገድ የግንባታ ሥራዉ ተጠናቆቅ ጥቅምት 14 ቀን 2003 ዓ.ም. ተመርቋል ፡፡
ግንባታዉ አገር በቀል የሥራ ተቋራጭ በሆነዉ በአኪር ኮንስትራክሽን የተከናወነዉ ይህዉ መንገድ ከ179.9 ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀ ሲሆን፤ አጠቃላይ ወጪዉም በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኗል፡፡ የፕሮጀክቱን የምህነድስና ቁጥጥርና የማማከር ስራ መታፈሪያ ኮንሰልቲንግ ኃ/የተ/የግ/ኩ የተባለ አገር በቀል ድርጅት አከናዉኖታል ፡፡