Register  
Wednesday, February 22, 2012
Home » Communication » Report  

 

Minimize

  • ERA Bridges
  • ERA at Road Construction
  • Bridges
  • Addis - Adama Supper Highway

የ2003 በጀት ዓመት የአራተኛ ሩብ ዓመት እና የአስራ ሁለት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት

Minimize

                                                                                                  ሐምሌ 2003

በ2003 በጀት ዓመት ኢመባ የመደበኛ ጥገና ሥራዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 19175.5 ኪ.ሜትር የሚሸፍን የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወን ዕቅድ የያዘ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1747 ኪ.ሜትር የመንገዶች ማጠናከር ማሻሻል እና ግንባታ 640.5 ኪ.ሜትር የመንገዶች ወቅታዊ ጥገና እና 16788 ኪ.ሜትር በልዩ ልዩ መንገዶች ላይ የመደበኛ ጥገና ሥራዎች ይገኙበታል:: ከዚህ በተጨማሪ 16 የፖሊሲ ድጋፍ እና አቅም ግንባታ 28 የፊዚቢሊቲ የአካባቢ ተዕኖ ፤የዲዛይንና የዲዛይን ክለሳ ጥናቶች እንዲሁም 8 የድልድዮች ግንባታ እና የተለያዩ የድልድይ ጥገና ፕሮጀክቶች በዕቅድ ውስጥ ተካተዋል::

በበጀት ዓመቱ ከላይ የተጠቀሱትን ሥራዎች ማስፈፀሚያ የመደበኛ በጀትን ጨምሮ ብር 13.6 ቢሊዮን ተመድል ከዚህ ውስጥ ብር 12.8 ቢሊዮን ከመንግስት ካዝና ፤ከብድርና ከዕርዳታ ለካፒታል ኘሮጀክቶች ፤ብር 71.6 ሚሊዮን ከመንግስት ካዝና ለመደበኛ በጀት እንዲሁም ብር 715 ሚሊዮን ከመንገድ ፈንድ ለመደበኛና ወቅታዊ የመንገድ ጥገና ተመድቧል በመቀጠልም ኢመባ በታህሳስ እና ሰኔ ወራት በአቀረበው ጥያቄ መሠረት ብር 1.7 ቢሊዮን እና ብር 72.5 ሚሊዮን ተጨማሪ በጀት ከመንግስት ካዝና (ትሬዠሪ) ተፈቅዶለታል፡፡ በዚህም መሠረት የኢመባ ጠቅላላ ዓመታዊ በጀት ብር 15.4 ቢሊዮን ሆኗል፡፡

                                       ሙሉ ሪፖርቱን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Copyright 2011 - Ethiopian Roads Authority   |  Privacy Statement  |  Terms Of Use