Skip to Content
Amharic English

ዜና ዜና

Back

መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን የሊማሊሞ መንገድን የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው።

መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን  የሊማሊሞ መንገድን  የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው።

ፕሮጀክቱ የደባርቅ - ዛሪማ ሊማለሞ ተለዋጭ መንገድ ሲሆን 68.62 ኪ.ሜ ርዝመት አለው፡፡ እስካሁኑ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል የአፈር ጠረጋ ፣ድልዳሎ እና ሙሌት ስራዎች አንዲሁም እስከ 20 ሜትር እርዝመት ያለው የአፈር  የቆረጣ ስራ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም  የሶስት ትልልቅ ድልድዮች ግንባታ ስራ  ፣ የውሃ መፋሰሻ ቱቦዎች እና ቦዮች  ምርት ስራም እየተከናወነ ነው ፡፡ በቀጣዩ አመት የአስፋልት ንጣፍ  ስራ ለመጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ  ይገኛል፡፡

የደባርቅ - ዛሪማ ሊማለሞ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት ስራን በሚፈለገው ፍጥነት ለማካሄድ እክል የነበሩትን የሲሚንቶ እጥረት እና በከተሞች አካባቢ የሚስተዋሉ ወሰን ማሰከበር ችግሮችን ለመቅረፍ ኢመባ  ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር በትብብር እየሰራ  ነው።የደባርቅ - ዛሪማ መንገድ ዲዛይን እና ግንባታን  ባካተተ መልኩ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው የሚገነባው ፡፡ የመንገዱ ጎን ስፋት በወረዳ 21  እና  በገጠር 10 ሜትር ስፋት አለው ፡፡

የግንባታ ስራውን  2.14 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ እያካሄደ የሚገኝው ቤይጂንግ ኧርባን ኮንስትራክሽን ግሩፕ የተባለ የቻይናው አለም አቀፍ ተቋራጭ  ነው፡፡ 
የማማከር ስራው ደግሞ በባንግላዲሹ ቢ ሲ ኤል ከአገር በቀሉ  አይኮን ጋር  በትብብር ያካሂዱታል፡፡ የመንገዱ መገንባት ከአዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር አድርጎ ሽሬ የሚዘልቀው ዋና መንገድ አካል ከመሆኑም ባሻገር ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ደረጃውን በጠበቀ አስፋልት መንገድ የሚያገናኝ ስለሚሆን  ጠቀሜታው ከፍ ያለ  ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከደባርቅ አድርጎ ዛሪማ ለመሄድ የነበረውን ነባሩን የሊማሊሞ አደገኛ  መንገድ ከትራፊክ አደጋ፣ ከመሬት መንሸራተት እና  በክረምት ወቅት ሊከሰት ከሚችል  መንገድ መዘጋት በማስቀረት የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡

በተጨማሪም ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ተጠቃሚ ያልነበረውን የአካባቢውን ነዋሪ በዘመናዊ መንገድ  እንዲገለግል በማድረግ እንዲሁም በመስመሩ የሚመረቱትን የሰብል ውጤቶች በቀላሉ ወደገበያ በማቅረብ  አርሶ አደሩን  ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ፡፡ ወደ ሰሜን ተራሮች ለሚሄዱ ቱሪስቶች ምቹ መንገድ ከማቅረብ አንጻር ለቱሪዘም ሴከተሩም የበኩሉን ሚና ያበረከታል ። የመንገድ ፕሮጀክቱ ከነባሩ ሊማሊሞ መንገድ በስተግራ በኩል እየተሰራ   ሲሆን መነሻውን  ደባርቅ መሃል ከተማ   ያደርግና የዘበና፣ የቢጢቆ፣ የጫንቅ፣ የአደማራ ጊዮርጊስ፣ የአብረሃም፣ የአዳጋት፣ የጥርሃይና የማይጥምቀት እና  አምበራ ትናንሽ የቀበሌ አስተዳደር መቀመጫዎችን አቋርጦ ዛሪማ ከተማ ላይ ያበቃል፡፡  

ከተገነባ 82 ዓመታትን የተሻገረው ታሪካዊው የሊማሊሞ መንገድ በቀጣይ  የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ አካል በመሆን እራሱን የቻለ የቱሪስት መዳረሻ እና ሳይክል ጉዞ  ለሚያደርጉ የሀገር ውስጥና  የውጭ አገር ቱሪስቶች አይነተኛ መዳረሻ ቦታ ይሆናል ተበሎም ታቅዷል ፡፡


ተነቀሳቃሽ ምስል ተነቀሳቃሽ ምስል

HAWASSA -CHUKO HAWASSA -CHUKO

የሀዋሳ - ጩኮ 66 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ ።

የሞምባሳ - ናይሮቢ - አዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሀዋሳ - ጩኮ 66 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ስራ ተጠናቀቀ። አጠቃላይ የፕሮጀክቱን የማጠቃለያ ስራን የተመለከተ የመስክ የስራ ስምሪት በስፍራው ተካሂዷል ። በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባው የሀዋሳ - ጩኮ መንገድ በመስመሩ ላይ የሚገኙትን ከተሞች ፣ የእርሻና የኢንዱስትሪ ዞኖች እንዲሁም የቱሪስት መስህብ የሆኑ ስፍራዎችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በማስተሳሰር የጉዞ ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP

የህትመት ዉጤቶች የህትመት ዉጤቶች

የስራ ሂደት የስራ ሂደት