Skip to Content
Amharic English

ዜና ዜና

የወላይታን እና ዳውሮ ዞኖችን በአስፋልት ኮንክሪት መንገድ የሚያስተሳስረው የሶዶ-ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ ነው።

የወላይታን እና ዳውሮ ዞኖችን በአስፋልት ኮንክሪት መንገድ የሚያስተሳስረው የሶዶ-ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ ነው። 76 ኪ. ሜትር የሚረዝመው የሶዶ -ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት   ከአጠቃላይ ኪ. ሜትር ውስጥ 95 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በቀጣይ ሁለት ወራት ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል።  አካባቢው ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት እና ናዳ ለመከላከል በሚያስችል መልኩ ሰፋፊ የአቃፊ ግንብ እና የጋብዮን ስራዎች ተከናውነዋል። የሶዶ -ኦሞ ወንዝ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ አድጎ የተገነባ ነው።  የመንገድ ፕሮጀክቱ ከሶዶ ከተማ 7 ኪ. ሜትር ላይ... Read More About የወላይታን እና ዳውሮ ዞኖችን በአስፋልት ኮንክሪት መንገድ የሚያስተሳስረው የሶዶ-ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ ነው። »

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሞጆ - ሃዋሳ የክፍያ ፍጥነት መንገድ አካል የሆነውን የሞጆ - መቂ - ባቱ ምዕራፍ አንድ /92 ኪሜ /የመንገድ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ  የሞጆ - ሃዋሳ የክፍያ ፍጥነት መንገድ አካል የሆነውን የሞጆ - መቂ - ባቱ ምዕራፍ አንድ /92 ኪሜ /የመንገድ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ። በመርሃ-  ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክት ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣  የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/  ርእሰ መስተዳድር አቶ ዕርስቱ ይርዳው  ፣ የትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ፣የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ፣  ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች ታድመዋል፡፡ የፍጥነት መንገዱ የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ... Read More About ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሞጆ - ሃዋሳ የክፍያ ፍጥነት መንገድ አካል የሆነውን የሞጆ - መቂ - ባቱ ምዕራፍ አንድ /92 ኪሜ /የመንገድ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ። »

መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን የሊማሊሞ መንገድን የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው።

መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን  የሊማሊሞ መንገድን  የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው። ፕሮጀክቱ የደባርቅ - ዛሪማ ሊማለሞ ተለዋጭ መንገድ ሲሆን 68.62 ኪ.ሜ ርዝመት አለው፡፡ እስካሁኑ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል የአፈር ጠረጋ ፣ድልዳሎ እና ሙሌት ስራዎች አንዲሁም እስከ 20 ሜትር እርዝመት ያለው የአፈር  የቆረጣ ስራ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም  የሶስት ትልልቅ ድልድዮች ግንባታ ስራ  ፣ የውሃ መፋሰሻ ቱቦዎች እና ቦዮች  ምርት ስራም እየተከናወነ ነው ፡፡ በቀጣዩ አመት የአስፋልት ንጣፍ  ስራ ለመጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ  ይገኛል፡፡ የደባርቅ - ዛሪማ ሊማለሞ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት ስራን በሚፈለገው ፍጥነት... Read More About መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን የሊማሊሞ መንገድን የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው። »

​Ethiopian Roads Authority officials visit Sheger beautification and Entoto Park projects.

Ethiopian Roads Authority officials visit Sheger beautification and Entoto Park projects. Director General of the Ethiopian Roads Authority, Mr. Habtamu Tegegn, on the occasion said the Authority is proud to have left its mark on this great national project. He further said that Imba will continue to participate in the Halala Kela-Chebera Chirchara-Gibe III-Koisha Integrated Development Project, which is one of the planned projects in Gebeta. It is said that the project will play an... Read More About ​Ethiopian Roads Authority officials visit Sheger beautification and Entoto Park projects. »

204.8 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የጋሸና-ላሊበላ-ሰቆጣ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

የጋሸና-ላሊበላ-ሰቆጣ መንገድ አካል የሆነው የጋሸና-ቢልባላ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ከአጠቃላይ 105 ኪ.ሜ ርዝመት ውስጥ 87 በመቶ የደረሰ ሲሆን በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። የጋሸና-ቢልባላ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ በአሁኑ ወቅት 78 ኪ.ሜትሩ የአስፋልት ንጣፍ ስራው ተከናውኗል። ፕሮጀክቱን 1.87 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው አለማቀፉ ቻይና ሬል ዌይ ኢንጅነሪንግ ቁጥር 3 የስራ ተቋራጭ ነው።  የማማከርና የቁጥጥር ስራውን  ኢንጂነር ዘውዴ  እና  ዋይ ኤል ኤስ ኢንጂነሪንግ  አማካሪ ድርጅቶች በጣምራ እያከናወኑት ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም 99.8 ኪ.ሜትር የሚዘልቀው የመንገድ የፕሮጀክቱ ቀጣይ ክፍል የሆነው የቢልባላ-ሰቆጣ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከአጠቃላይ የግንባታ ስራ... Read More About 204.8 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የጋሸና-ላሊበላ-ሰቆጣ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ »

ተነቀሳቃሽ ምስል ተነቀሳቃሽ ምስል

HAWASSA -CHUKO HAWASSA -CHUKO

የሀዋሳ - ጩኮ 66 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ ።

የሞምባሳ - ናይሮቢ - አዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሀዋሳ - ጩኮ 66 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ስራ ተጠናቀቀ። አጠቃላይ የፕሮጀክቱን የማጠቃለያ ስራን የተመለከተ የመስክ የስራ ስምሪት በስፍራው ተካሂዷል ። በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባው የሀዋሳ - ጩኮ መንገድ በመስመሩ ላይ የሚገኙትን ከተሞች ፣ የእርሻና የኢንዱስትሪ ዞኖች እንዲሁም የቱሪስት መስህብ የሆኑ ስፍራዎችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በማስተሳሰር የጉዞ ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡

FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP

የህትመት ዉጤቶች የህትመት ዉጤቶች

የስራ ሂደት የስራ ሂደት