Skip to Content
Amharic English

NEWS NEWS

Back

የወላይታን እና ዳውሮ ዞኖችን በአስፋልት ኮንክሪት መንገድ የሚያስተሳስረው የሶዶ-ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ ነው።

የወላይታን እና ዳውሮ ዞኖችን በአስፋልት ኮንክሪት መንገድ የሚያስተሳስረው የሶዶ-ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ ነው።

76 ኪ. ሜትር የሚረዝመው የሶዶ -ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት   ከአጠቃላይ ኪ. ሜትር ውስጥ 95 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በቀጣይ ሁለት ወራት ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ ክፍት ይሆናል።  አካባቢው ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት እና ናዳ ለመከላከል በሚያስችል መልኩ ሰፋፊ የአቃፊ ግንብ እና የጋብዮን ስራዎች ተከናውነዋል።

የሶዶ -ኦሞ ወንዝ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ አድጎ የተገነባ ነው።
 የመንገድ ፕሮጀክቱ ከሶዶ ከተማ 7 ኪ. ሜትር ላይ ተነስቶ ኦሞ ወንዝ ላይ የሚያበቃ ሲሆን የግንባታው መጠናቀቅ ወደ ግልገል ጊቤ 3 የኤሌትሪክ ማመንጫ ግድብ በተፈለገው ፍጥነት ለመድረስ ከማስቻሉም በላይ ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው ።
 
በአካባቢው የሚገኘውን የሰብል ምርቶች የሆኑትን ማሽላ ፣ የእንሰት ውጤቶች በተጨማሪም የአሳ ምርቶችን ትራንስፖርትን ተጠቅሞ ወደ ማዕከላዊ ገበያ በተሻለ ዋጋ በመሸጥ አምራች ሸማቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። ቀደም ሲል ከሶዶ ተነስቶ የኦሞ ወንዝ ለመድረስ መንገዱ ምቹ ባለመሆኑ ከ2 ሰዓት በላይ  ይወስድ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓት በተሽከርካሪ የሚደረገውን የትራንስፖርት ጉዞ በአማካኝ በግማሽ ቀንሷል። ለአጠቃላይ ግንባታው ከአንድ ቢሊየን ሶስት መቶ አርባ ስምንት ሚሊየን ብር በላይ የጠየቀ ሲሆን ሙሉ ወጪውም በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው ።

ሁናን ሁንዳ ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን የተባለው የቻይና ኩባንያ ግንባታውን እያከናወነው ሲሆን የማማከርና የቁጥር ሥራውን ደግሞ የተባበሩት የምህንድስና አማካሪ ኃ/የተ/የግ/ማ እያካሄደው ይገኛል።የመንገድ ፕሮጀክቱ የጎን ስፋት በወረዳ 21.5 ሜትር በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በገጠር የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 1ዐ ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው የተገነባው።


CALL FOR PAPER CALL FOR PAPER

HAWASSA -CHUKO HAWASSA -CHUKO

Hawassa-Chuko 66 km asphalt concrete road construction project completed

The Hawassa-Chuko 66 km asphalt concrete road, part of the Mombasa-Nairobi-Addis Ababa road corridor, has been completed.Field recruitment for the overall project was completed on site.The Hawassa-Chuko road, built on asphalt concrete, will significantly reduce travel time and cost by modernizing the towns along the route, agricultural and industrial zones, and tourist attractions.

FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP