Skip to Content
Amharic English

NEWS NEWS

Back

ዳዬ - ጭሬ - ናንሴቦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ይገኛል

ዳዬ - ጭሬ - ናንሴቦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም  ሂደት ላይ ይገኛል 

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢ መ አ) የሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎችን በቅርበት የሚያስተሳስረው የዳዬ-ጭሬ-ናንሴቦ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አሁናዊ የግንባታ አፈጻጸም 84 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በቅርቡ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡የመንገድ ግንባታዉ አጠቃላይ 71.4 ኪ.ሜትር ርዛማኔ ያለዉ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 47 ኪ.ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ አብዛኛዉ የቅድመ አስፋልት ንጣፍ ስራው እየተገባደደ ነው። ቀሪ የአስፋልት ንጣፍ ስራውም በቅርቡ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ለግንባታው የሚውለው  1,723,608,313 ብር  ሲሆን ይህ ወጪ የሚሸፍነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው። የመንገድ ፕሮጀክቱ  ከአዲስ አበባ 404 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ዳዬ ከተማ መነሻውን በማድረግ በኦሮሚያ ክልል እየተገነባ ከሚገኘው የኤዶ-ሴሮፍታ-ወርቃ መንገድ ፕሮጀክት ጋር ይገናኛል። የመንገድ ፕሮጀክቱ የሚካሄድበት አካባቢ የተራዘመ ዝናብ የሚዘንብበት በመሆኑ የግንባታ ሂደቱ በታሰበለት ፍጥነት እንዳይሄድ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ 

በተጨማሪም የወሰን ማስከበር እና ተያያዥ ችግሮች ፣ የዋጋ ንረትና የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ችግሮች በግንባታ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ግንባታዉ በሚካሄድበት አካባቢ ሲስተዋል የቆየው የመሬት መንሽራተት ለግንባታዉ መዘግየት ሌላኛዉ ፈተና ነበር፡፡ ሆኖም ግን አሁን ላይ በአካባቢው የሚስተዋለው የዝናብ ሁኔታ በመቀነሱ እና በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሻሸመኔ እና አካባቢው ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና በኢመአ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ በመሆኑ ችግሮቹ ከሞላ ጎደል ተቀርፈዉ አሁን ላይ አፈፃፀሙ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ መንገዱ  ትከሻን ጨምሮ በገጠር 10 ሜትር እና በከተማ 19 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረዉ ተደርጎ ነዉ እየተገነባ የሚገኘዉ፡፡  ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ቻይና ዉ ይ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ  ሲሆን ፣ ክላሲክ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን በማከናወን ላይ ይገኛል ፡፡ የቀድሞ የመንገዱ ይዘት በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነበር። ይህ ፕሮጀክት ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ሲዳማ ክልልን ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመንገድ መሰረት ልማት በቅርበት ያስተሳስራል። በተጨማሪ አካባቢው  ቡናን ጨምሮ ሌሎች የአዝርዕት ምርቶች የሚመረቱበት በመሆኑ አርሶ አደሮች ያመረቱትን ምርት በቀላሉ ወደ ገቢያ እንዲያደርሱ ይረዳቸዋል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በንሳ፣ዳኤላ፣ጭሪ እና ነንሰቦ የሚባሉ ወረዳዎችን እና በርካታ ትናንሽ ከተሞችን  በቅርበት የሚያስተሳስር በመሆኑ የከተሞች እድገት እንዲፋጠን ያደርጋል።

በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et


CALL FOR PAPER CALL FOR PAPER

HAWASSA -CHUKO HAWASSA -CHUKO

Hawassa-Chuko 66 km asphalt concrete road construction project completed

The Hawassa-Chuko 66 km asphalt concrete road, part of the Mombasa-Nairobi-Addis Ababa road corridor, has been completed.Field recruitment for the overall project was completed on site.The Hawassa-Chuko road, built on asphalt concrete, will significantly reduce travel time and cost by modernizing the towns along the route, agricultural and industrial zones, and tourist attractions.

FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP