Skip to Content
Amharic English

NEWS NEWS

Back

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሞጆ - ሃዋሳ የክፍያ ፍጥነት መንገድ አካል የሆነውን የሞጆ - መቂ - ባቱ ምዕራፍ አንድ /92 ኪሜ /የመንገድ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ  የሞጆ - ሃዋሳ የክፍያ ፍጥነት መንገድ አካል የሆነውን የሞጆ - መቂ - ባቱ ምዕራፍ አንድ /92 ኪሜ /የመንገድ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ።


በመርሃ-  ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክት ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣  የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/  ርእሰ መስተዳድር አቶ ዕርስቱ ይርዳው  ፣ የትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ፣የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ፣  ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ባለስልጣናት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች ታድመዋል፡፡ የፍጥነት መንገዱ የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር  አካል ሲሆን  የኢትዮጵያን የወጪ ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን  በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም የሚያስች ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ።

 ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያስተሳስሩ የመንገድ መሰርተ ልማት ግንባታ በስፋት እየተከናወነች  እንደሆነና  ከአዳማ አዋሽ የሚዘልቀው መንገድ በቅርቡ በፍጥነት መንገድ ደረጃ የግንባታ ስራው እንደሚጀመርም አብስረዋል። የትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ  የምዕራፍ አንድ የሞጆ መቂ ባቱ   መንገድ በቀጣይ በመስመሩ ላይ የሚገኙትን ወረዳዎች ፣ ከተሞች አማራጭ መንገድ ተጠቃሚ በማድረግና በግብርና  በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ  የትራፊክ እንቅስቃሴውን ምቹ  ስለሚያደርግ  ሁለንተናዊ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

 ዘመናዊና ፈጣን  መንገድ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ከሚኖረው ፋይዳ አንፃር ከተለያዩ ሀገሮች የቀሰምነውን ልምድና ተሞክሮ መነሻ በማድረግ መንግስት   በቀጣይ ከፍተኛ በጀት ለዘርፉ በመመደብ የፍጥነት መንገድ የማስፋፋቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው የፍጥነት መንገዱ የግብርና ምርታማነትን  በመስመሩ የሚገኙትን ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለጎብኚዎች ተደራሽ በማድረግ   እረገድ ዘርፈ ብዙ ሚና እንዳለው  ተናግረዋል።

በመንገዱ ክልል ውስጥ ያሉ  ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ላሉ እና   በቀጣይ ለመገንባት በታቀዱ ግዙፍ የኢንዱስትሪ እና የአግሮፕሮሰሲንግ ፓርኮች ደረጃቸውን የጠበቀ መንገዶችን በማቅረብ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በሚደረገው ጥረት  የፍጥነት መንገዱ ጉልህ ሚናን እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ በበኩላቸው የመንገዱ የግንባታ ስራ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር  ወጪን እንደጠየቀ ተናግረዋል።

 አውስተው የሞጆ መቂ ባቱ  የክፍያ የፍጥነት መንገድ ከነባሩ መንገድ ትይዩ በአዲስ መልክ ከእንስሳት እና ከሰዎች እንቅስቃሴ ነጻ በሆነ መልኩ የተገነባ እንደሆነም እና ከአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ በመቀጠል ለአገራችን  ሁለተኛው ፍጥነት መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የፍጥነት  መንገዱ  አራት መኪኖችን በአንድ ጊዜ በግራና በቀኝ በኩል የሚያስተናግ ሲሆን ግንባታው  የክፍያ ጣቢያን ጨምሮ የተሸከርካሪ ሚዛን ቁጥጥር ጣቢያዎች እና በተለያዩ ቦታዎች  የሬስቶራንት አገልግሎት መስጫ  ፣ የተሽከርካሪ ጥገና ማከናወኛ  (ጋራዥ) እና ለመንገዱ ተጠቃሚዎች የሚረዱ  የተለያዩ አገልግሎት መስጫ መዕከላት የሚያካትት ነው ብለዋል።

የምዕራፍ አንድ የሞጆ - መቂ - ባቱ የክፍያ የፍጥነት መንገድ በሁለት ኮንትራት የተከፈለ ሲሆን አሱም ሞጆ - መቂ 56  ኪሜ እና መቂ -ባቱ 36 ኪ.ሜ ናቸው ፡ ከዛም ባለፈ 10 ሺ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ከግብጽ ካይሮ ተነስቶ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ድርስ የተዘረጋው የታላቁ የትራንስ አፍሪካን ሃይዌይ የመንገድ ትስስር ክፍልም ነው ፡፡ ከዚህም ውስጥ ለኮንትራት አንድ ሞጆ - መቂ በአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ ፋይናስ የ4,219,913,161.65 ቢሊዮን ብር ብድር እና በኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ በጀት የተሸፈነ ነው ፡፡

ቀጣዩ ምዕራፍ አንድ ኮንትራት ሁለት ከመቂ እስከ ባቱ ያለው መንገድ የተገነባው በ2, 132 547,087.55 ቢሊዮን ብር ሲሆን የኮሪያው ኤግዚም ባንክ (በብድር) እና ከኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ በጀት  ወጪው  ተሸፍኗል፡፡ ኮንትራት አንድ  የሞጆ- መቂ የክፍያ ፈጣን መንገድ ግንባታ ስራ ያከናወነው የስራ ተቋራጭ  ቻይና ሬል ዌይ ሰቨንዝ  ግሩፕ ነው፡፡

 የማማከር እና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ሊ ኢንተርናሽናል ሊሚትድ ካናዳ ከ ሊ አሶሲየት ሳውዝ ኤሲያ ፕራይቬት ሊሚትድ በጥምርት ሲሆን ዩናይትድ ኮንሰልት ኢንጅነርስ በንኡስ ተቋራጭነት ተሳትፏል፡፡ ኮንትራት ሁለት መቁ - ባቱ መንገድ የተገነባው በኮርያው ዴዎ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ነው፡፡ 

የማማከር ስራውን የተከናወነው ደግሞ ኪዮንግዶንግ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ ፣ ኩንህዋ ኢንጂነሪንግ እና ኮንሰልቲንግ ኮርፖሬሽን ካንፓኒ ፣ ዶንግ ኢል ኢንጂነሪንግ  ኮንሰልታንትስ ሊሚትድ ካምፓኒ ከኢትዮ ኢንፍራ ኢንጂነሪንግ  እና ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ፒ ኤል ሲ በጋራ በመሆን ነው፡፡
ከሞጆ እስከ ባቱ በተዘረጋው 92 ኪሜ ውስጥ  6 ያህል ከነባሩ መንገድ ጋር የሚያገናኙ ማሳለጨዎች ተገንብቶለታል፡፡
  ከዚህም በተጨማሪ   ለእግረኛ  ከመንገድ በታች እና በላይ  መተላለፊያ  45 መተላለፊያ አሉት ፡፡

 በተመሳሳይ መልኩ ተሸከርካሪዎች የሚጠቀሙበት  14 የተመረጡ ቦታዎች የመተላለፊያ  የግንባታ ስራ ተካሂዶለታል፡፡በአጠቃላይ ሞጆ መቂ ባቱን ጨምሮ  ሃዋሳ ድረስ የሚዘልቀው 202 ኪ .ሜ የፍጥነት  መንገድ የጎን ስፋቱ  32 ሜትር ነው፡፡ የመንገድ አካፋዩ በዚህ ደረጃ እንዲሰፋ የተደረገው በተቃራኒ አቅጣጫ ያለን ተሸከርካሪን በመለየት አደጋን ለማስወገድ አልያም ለመቀንስ  ነው፡፡  የመንገዱ አጠቃላይ ወሰን 90 ሜትር ስፋት ያለው  ነው፡፡  ይህም በቀጣይ ለሚኖረው የማስፋፋት ስራ በቂ ቦታ እንዲኖር የሚያስችል ይሆናል፡፡

 በተጨማሪም የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን መሰረት ባደረገ መልኩ ችግኞች ይተከሉለታል፡፡ በፍጥነት መንገዱ ለመጠቀም የተቀመጠለት የፍጥነት ገደብ በሰአት ከ80 እስከ 120 ኪሜ ነው፡፡ ከዛም ባለፈ በነባሩ መንገድ ተደጋጋሚ ብልሽት ሳቢያ ለአላስፈላጊ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ይወጣ የነበረው ወጪ ከመቀነሱም ባለፈ በትራፊክ  መጨናነቅ ምክንያት ያለአግባብ ይወጣ የነበረውን የነዳጅ ፍጆታን የሚያስቀር ነው፡፡ ከዛም ባለፈ 10 ሺ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ከግብጽ ካይሮ ተነስቶ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ድርስ የተዘረጋው የታላቁ የትራንስ አፍሪካን ሃይዌይ የመንገድ ትስስር አካል ነው ፡፡


CALL FOR PAPER CALL FOR PAPER

HAWASSA -CHUKO HAWASSA -CHUKO

Hawassa-Chuko 66 km asphalt concrete road construction project completed

The Hawassa-Chuko 66 km asphalt concrete road, part of the Mombasa-Nairobi-Addis Ababa road corridor, has been completed.Field recruitment for the overall project was completed on site.The Hawassa-Chuko road, built on asphalt concrete, will significantly reduce travel time and cost by modernizing the towns along the route, agricultural and industrial zones, and tourist attractions.

FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP