Top News Top News

Back

የላሊበላ - ኩልመስክ - ሙጃ መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል

የላሊበላ - ኩልመስክ - ሙጃ መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 03፣ 2016 (ኢ መ አ) ፡- የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት መዳረሻ የሆነው የላሊበላ - ኩልመስክ - ሙጃ መንገድ ፕሮጀክት አሁን ላይ በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል።ፕሮጀክቱ 48 ነጥብ 78 ኪሎሜትር የሚሸፍን ኾኖ፣ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ በመንገድ ግንባታው እስከ አሁን የካምፕ ግንባታ፣ የዲዛይን፣ የአፈር ጠረጋ፣ ቆረጣ እና ሙሌት፣ የውኃ ተፋሰስ እንዲሁም የቅድመ-ምርት ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ የግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም በአሁን ወቅት 10 ነጥብ 51 በመቶ ደርሷል፡፡ በተጨማሪም የአነስተኛ እና ከፍተኛ ከልቨርቶች፣ የአስፋልት ንጣፍ እንዲሁም የስድስት ድልድዮች ግንባታ ሥራም በፕሮጀክቱ ተካትቷል፡፡  ዓለም አቀፉ ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪነግ ኮንስትራክሽን ኮራፖሬሽን ግንባታውን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ቤዛ ኢንጅነሪንግ ኬኒያ ሊሚትድ የግንባታውን ጥራት የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ ይሠራል፡፡ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 1,888,292,297 (1 ነጥብ 8 በሊዮን) ብር በፌደራል መንግስት ተመድቧል፡፡ 

በአካባቢው አልፎ አልፎ የሚስተዋለው የጸጥታ ስጋት፣ በመንገድ ክልል ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች በወቅቱ አለመነሳት እንዲሁም የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እጥረት እና ዋጋ መናር በግንባታው ሂደት ውስጥ የገጠሙ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ ችግሮቹን ለመፍታት የአትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከየአካባቢው ማኅበረሰብ እና የመስተዳድር አካላት ጋር በመቀናጀት ጥረት በመደረጉ አሁን ላይ ግንባታው በመልካም ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የመንገዱ ነባር ገጽታ በጠጠር መንገድ ደረጃ ሲኾን፥ በአገልግሎት ብዛት በእጅጉ የተጎዳ ነው፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ በተለይም የላሊበላ ፍልፍል አብያተ-ክርስቲያናት አማራጭ መዳረሻ በመኾን ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ በሥፍራው የሚመረቱትን የዘንጋዳ፣ ገብስ፣ ባቄላ እና መሰል የግብርና ምርት ውጤቶች ወደ ማዕከላዊ ገበያ በቀላሉ ለማድረስ ያስችላል፡፡ የላሊበላ፣ ኩልመስክ እና ሙጃ ከተሞችን ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ያስተሳስራል፡፡


በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et


what is new? what is new?