Top News
ዳዬ - ጭሬ - ናንሴቦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ይገኛል
ዳዬ - ጭሬ - ናንሴቦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢ መ አ) የሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎችን በቅርበት የሚያስተሳስረው የዳዬ-ጭሬ-ናንሴቦ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አሁናዊ የግንባታ አፈጻጸም 84 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በቅርቡ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡የመንገድ ግንባታዉ አጠቃላይ 71.4 ኪ.ሜትር ርዛማኔ ያለዉ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 47 ኪ.ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ አብዛኛዉ የቅድመ አስፋልት ንጣፍ ስራው እየተገባደደ ነው። ቀሪ የአስፋልት ንጣፍ ስራውም በቅርቡ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ለግንባታው የሚውለው 1,723,608,313 ብር ሲሆን ይህ ወጪ የሚሸፍነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው። የመንገድ ፕሮጀክቱ ከአዲስ አበባ 404 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ዳዬ ከተማ መነሻውን በማድረግ በኦሮሚያ ክልል እየተገነባ ከሚገኘው የኤዶ-ሴሮፍታ-ወርቃ መንገድ ፕሮጀክት ጋር ይገናኛል። የመንገድ ፕሮጀክቱ የሚካሄድበት አካባቢ የተራዘመ ዝናብ የሚዘንብበት በመሆኑ የግንባታ ሂደቱ በታሰበለት ፍጥነት እንዳይሄድ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡
በተጨማሪም የወሰን ማስከበር እና ተያያዥ ችግሮች ፣ የዋጋ ንረትና የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ችግሮች በግንባታ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን አሳድረዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ግንባታዉ በሚካሄድበት አካባቢ ሲስተዋል የቆየው የመሬት መንሽራተት ለግንባታዉ መዘግየት ሌላኛዉ ፈተና ነበር፡፡ ሆኖም ግን አሁን ላይ በአካባቢው የሚስተዋለው የዝናብ ሁኔታ በመቀነሱ እና በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሻሸመኔ እና አካባቢው ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና በኢመአ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ በመሆኑ ችግሮቹ ከሞላ ጎደል ተቀርፈዉ አሁን ላይ አፈፃፀሙ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡ መንገዱ ትከሻን ጨምሮ በገጠር 10 ሜትር እና በከተማ 19 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረዉ ተደርጎ ነዉ እየተገነባ የሚገኘዉ፡፡ ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ቻይና ዉ ይ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ ሲሆን ፣ ክላሲክ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን በማከናወን ላይ ይገኛል ፡፡ የቀድሞ የመንገዱ ይዘት በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነበር። ይህ ፕሮጀክት ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ሲዳማ ክልልን ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመንገድ መሰረት ልማት በቅርበት ያስተሳስራል። በተጨማሪ አካባቢው ቡናን ጨምሮ ሌሎች የአዝርዕት ምርቶች የሚመረቱበት በመሆኑ አርሶ አደሮች ያመረቱትን ምርት በቀላሉ ወደ ገቢያ እንዲያደርሱ ይረዳቸዋል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በንሳ፣ዳኤላ፣ጭሪ እና ነንሰቦ የሚባሉ ወረዳዎችን እና በርካታ ትናንሽ ከተሞችን በቅርበት የሚያስተሳስር በመሆኑ የከተሞች እድገት እንዲፋጠን ያደርጋል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
what is new?
- የላሊበላ - ኩልመስክ - ሙጃ መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል
- የደብረብርሃን - አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ
- የኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ አፈጻጸም በመስክ ምልከታ ተቃኝቷል።
- መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን የሊማሊሞ መንገድን የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው።
- የወላይታን እና ዳውሮ ዞኖችን በአስፋልት ኮንክሪት መንገድ የሚያስተሳስረው የሶዶ-ኦሞ ወንዝ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ ነው።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሞጆ - ሃዋሳ የክፍያ ፍጥነት መንገድ አካል የሆነውን የሞጆ - መቂ - ባቱ ምዕራፍ አንድ /92 ኪሜ /የመንገድ ፕሮጀክትን በይፋ መረቁ።
- Ethiopian Roads Authority officials visit Sheger beautification and Entoto Park projects.
- The 204.8 km Gashena-Lalibela-Sekota asphalt concrete road is going to completion.
- The Prime Minister of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, Dr. Abiy Ahmed, today officially started the construction of the Lake Bistima-Chifra asphalt concrete road.
- The Eteya-Robe road construction project has begun.