News News

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለ2010 በጀት ዓመት የተመደበለት በጀትና የወጪ አጠቃቀሙን የሚያሳይ መረጃ

የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ታሳቢ

 አድርጎ በመስራት ብክነትን እንከላከል!

አገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሀድሶ በሚፈለገው ልክ ለማስቀጠል ና ከዜጎች ለሚነሱ የእኩልነት ና የፍትሀዊነት ጥያቄ በቂ መልስለ መስጠት በየደረጃው ጥረት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይም  በፋይናንስ ግልፀኝነት ና ተጠያቂነት ከፍ  ሲልም በመልካም አስተዳደር  ዙሪያ  የሚደረጉ  እንቅስቃሴዎች ለሕዝብ ተደራሽነታቸው እንዲጎለብት ሁሉም ተቋማት የበኩላቸውን ሀላፊነት መወጣት እንደሚኖርባቸው ይታመናል ፡፡ ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ና ለሚያስተዳድራቸው ሰራተኞች ደመወዝ ና እንዲሁም ልዩልዩ ወጪዎች የሚሆን በጀት እየተመደበለት የሚንቀሳቀስ መስሪያ ቤት መሆኑ ገልፅ ነው ፡፡ ስለሆነም መንግስት የሚመድብለትን በጀት በአግባቡ አቅዶ በትክክል መጠቀሙን ለባለድርሻ አካላትና  ለመንግስት ይፋ  ለማድረግ የሚያስችለውን አሰራር በስፋት እየሄደበት ይገኛል፡፡ የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ታሳቢ አድርጎ  መስራት ብክነትን ለመከላከል ብቻ ሣይሆን የርስበርስ የስራ ግንኙነትን በማጠናከር አገራዊ ራዕይ ሰንቀን ለተያያዝንው የዕድገት ግስጋሴ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ጥርጥር የለውም ፡፡ ይህም እንዲሆን በመጽሔት አምዳችን ተከታታይ የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን መሰረት ያደረጉ ጽሁፎችን የምናወጣ መሆናችንን እየገለጽን ፣ለዛሬው  ለመነሻ እንድትሆን ቀጥላ የቀረበችውን የበጀትና የአጠቃቀም ሂደትንየም ታሳይ አጭርና ጠቅለል ያለች የዘጠኝ ወር  የሂሳብሪፖርት   አቅርበናልና  እንዲመለከቷት በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

 

                                   ለኢትዮጵያ  መንገዶች  ባለስልጣን  ለ2010  በጀት  ዓመት

                                   የተመደበለት  በጀትና  የወጪ  አጠቃቀሙን የሚያሳይ መረጃ

                                             የመደበኛ በጀት ብር ------------  317,635,000

                                            የካፒታል  በጀት  ብር ------------45,532,184,000 

                                           በመንግስት  የተሸፈነ  በጀት--------35,000,000,000

                                           ከአበዳሪ ድርጅቶች  የተገኘ--------10,378,622,000

                                                   ከእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የተገኘ - 153,562,000       

                                           የጠቅላላ በጀት ድምር ብር ------- 45,849,819,000

                                          

 

                                       

 

ከሐምሌ 1/2010 በጀት  ዓመት እስከ መጋቢት 30/2010 / የ9 ወር / የፋይናንስ አጠቃቀም

 

 

    መግለጫ

 

ፕሮጄክት

 

የዓመቱ በጀት

 

የተከፈለ

 

በመቶኛ

ለመደበኛ  በጀት/  ለደመወዝና  ለሥራ  ማስኬጂያ /      

317,635,000

 

 

 

 

 250,226,250  

78.78

 

ከመጀመሪያው እስከ የሁለተኛው የሩብ ዓመት ያለው ጊዜ  የዝናብ ወቅት ስለሚሆን የመንገድ ግንባታና የጥገና ሥራ ጎልቶ የማይታይበት ሲሆን ባንፃሩ  የዝግጅትና ወደተጠናከረ ሥራ የሚገባበት  ሂደት ነው ፡፡

ከሦስተኛ እስከ አራተኛው የሩብ ዓመት  ደረቅና የፀሐይ ወቅት በመሆኑ  የመንገድ ግንባታም ሆነ የጥገና ሥራው ተጠናክሮ የሚከናወንበትና አብዛኛው የፋይናንስ ወጪ በከፍተኛ ደረጃ  የሚመዘገብበት ጊዜ ነው ፡፡

      ድምር     

317,635,000

 250226250  

 

ለካፒታል  በጀት  የተመደበ

45,532,184,000

 ------------------

 

  • ለዋና  መንገዶች  ማጠናከር

6,886,548,000

1,256,309,221 

18.24

  • ለዋናመንገዶች ደረጃ  ማሻሻል

1,512,629,000

669,071,511

44.23

  • ለመንገዶች ከባድ ጥገና

3,232,700,000

898,462,449

27.79

  • ለአገናኝ  መንገዶች  ደረጃ  ማሻሻል

10,856,357,000

3,921,755,559

36.12

  • ለአገናኝ  መንገዶች  ደረጃ  ግንባታ

21,458,812,000

11,198,861,288

52.18

  • ለድልድዮች  ግንባታ  ማጠናከር

395,000,000

99,676,508

25.23

  • ለፖሊሲድጋፍና  አቅም  ግንባታ

951,538,000

276,278,128

29.03

    ለዲዛይንለፊዚቢሊቲ እና የአካባቢ ተጽዕኖ  ጥናት

238,600,000

63,975,805

26.81

 

                                                 ድምር

 

45,532,184,000

 

18,497,064,476

 

 

40.62