News News

የ2010 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምን እና የቀጣዩ በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ፡፡

 

 2010 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምን እና የተጀመረውን 2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አስመልክቶ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ሃምሌ 30 ቀን 2010 . ውይይት አካሄዱ፡፡የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 2010 በጀት ዓመት አስራሁለት ወራት ዋና መንገዶችን በማጠናከር፣ዋና መንገዶችን ደረጃ በማሻሻል፣የአገናኝ መንገዶችን ደረጃ በማሻሻል፣በአገናኝ መንገዶች ግንባታ፣በመንገዶች ከባድ ጥገና፣በወቅታዊ የመንገድ ጥገና እና በመደበኛ ጥገና 18629.6 . የሚሸፍኑ ስራዎችን ለመስራት አቅዶ15533 . በማከናወን የዕቅዱን 83 በመቶ ለማሳካት ችሏል፡፡ባለስልጣን መስሪያቤቱ በተጠናቀቀው 2010 በጀት ዓመት በሁሉም የአገራችን ክፍሎች የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን ለማካሄድ አቅዶ ወደተግባር በመግባት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ወደተግባር ከተገባበት ጊዜጀምሮ በመንገድ ግንባታ ስራው ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ የተለያዩ ችግሮች የነበሩ ሲሆን፣ከነዚህም መካከል ከወሰን ማስከበር እና መሰልጉዳዮች ጋራ የተያያዙ ችግሮች ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ለመፈፀም እንዳይቻል ራሱን የቻለ ተፅዕኖ ሲፈጥሩ ቆይተዋል፡፡የባለስልጣን መስሪያቤቱ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቡድን ተደራጅተው በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ወደሚገኙ ፕሮጀክቶች በአካል በመሄድ ከአካባቢው የመስተዳደር አካላት፣የህብረተሰብ ተወካዮች እና የፕሮጀክት አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ችግሮቹን ለመፍታት ጥረት ቢደረግም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ይህን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ ባለመቻሉ በበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈፃፀም ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር እደቻለ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ከዚህም ባሻገር የመንገድ ግንባታ ስራው በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ የሚገኝ በመሆኑ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የነበሩ የፀጥታ ችግሮች በመንገድ ግንባታ ስራዎች ላይ ቀላል የማይባሉ ተፅዕኖዎችን ሲፈጥሩ ቆይተዋል፡፡በ2010 በጀት ዓመት የነበረው የአገር በቀል የስራተቋራጮች ተሳትፎ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፣በአፈፃፀም ደረጃም ከውጪ አገር የስራ ተቋራጮች የላቀ ማስመዝገብ መቻላችው ተገልጿል፡፡ባለስልጣን መስሪያቤቱ በሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በዋናነትት ኩረት ተደርጎባቸው እንዲፈፀሙ በዕቅድ የያዛቸው ዋና ዋና ስራዎች፡- ግንባታቸው ተጀምሮ የማይጠናቀቁ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ግንባታቸው በፍጥነት በተገቢው ጥራት እንዲጠናቀቁ የማድረግ፣የዲዛይን ጥናት የተካሄደላቸው እና እየተካሄደላቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ግንባታ የማስጀመር እና የበርካታ ፕሮጀክቶችን ዲዛይን ጥናት እንዲሁም የማስፈፀም አቅም ግንባታ ሥራዎች ለማካሄድ ዕቅዱን አቅዶ ወደተግባር ከገባ ሶስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ከዚህም ባሻገር ይህ የሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለመንገዶች ከባድ ጥገና እና ለአዲስ ዋና እና አገናኝ መንገዶች ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠበት ሲሆን፣በኢመባ ከተለዩ የአዲስ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በክልሎች ለተጠየቁት ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ሰፊ የሆኑ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡የሁለተኛዉ የዕድገት እና ትራንስፎርሜን ዕቅድ የሶስት ዓመት አፈፃፀምን ስንመለከት ዋና መንገዶችን በማጠናከር፣በዋና መንገዶች ደረጃ ማሻሻል፣አገናኝ መንገዶችን በማሻሻል፣በአዲስ ዋና/አገናኝ መንገዶች ግንባታ፣በፈጣን መንገድ ግንባታ እና በከባድ መንገዶች ጥገና ስራ 8582 ኪ.ሜ ለመሥራት ዕቅድ ተይዞ 8594.5 ኪ.ሜ ለማከናወን ተችሏል፡፡በዚህም መሰረት አጠቃላይ የሁለተኛዉ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን የሶስት ዓመት አፈፃፀም100% ሆኗል፡፡በአጠቃላይ ባለስልጣን መስሪያቤቱ በ2010 በጀት ዓመት የተመዘገቡ መልካም ውጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው በማድረግ እና ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን ደግሞ በመቅረፍ በ2011 በጀት ዓመት 3158 ኪሎሜትር የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማካሄድ ያቀደሲሆን፣ከዚህም በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ ከመንገድ ግንባታ ስራዎች ባሻገር የጥገና ስራዎችን አጠናክሮ የማስቀጠል ስራ፣የተጀመረው የሞደርናይዜሽን ጥናት ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የማድረግ እና ተቋማዊ ዕሴቶችን የማጠናከር ስራ በቁርጠኝነት የሚተገበር ይሆናል፡፡