Find Us

 

 
Likes

Top News Top News

Top News

የሞሮቾ- ዲምቱ- ቢተና- ሶዶ መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይነው::

የኢትዮጵያ መንግስት የቀረጸው የአራተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራም አካል የሆነው ኮንትራት አንድ የሞሮቾ- ዲምቱ- ቢተና እና ኮንትራት ሁለት ቢተና- ሶዶ መንገድ በያዝነው በጀት ዓመት መጨረሻ ድርስ ይጠናቀቃል:: ይህ መንገድ ለአስራር አመቺነት ሲባል በሁለት ኮንትራቶች ተከፍሎ የሚሰራ ሲሆን፣60.8 ኪ.ሜትር የሚሸፍነው የሞሮቾ- ዲምቱ- ቢተና ኮንትራት አንድ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከጠጠር መንገድ ወደ አስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲያድግ ተደርጎ በመገንባት ላይ ይገኛል::በተጨማሪ


 

የሶሮቃ-አብደራፊ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ከተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ቀድሞ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በአማራክልልውስጥየሚገኘውየሶሮቃ-አብረሃጂራ-አብደራፊ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታም እንዲሁ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህን መንገድ ግንባታ ለማካሄድ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘለት ሲሆን ፣ ይህ የግንባታ ሙሉ ወጪም በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው፡፡ ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው አገር በቀሉ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ሱር ኮንስትራክሽን ሲሆን ፣ ክላሲክ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ የግንባታውን የማማከርና የቁጥጥር ስራ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪ

 


የዳባት-አጅሬ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የዳባትናየፀገዴወረዳዎችንበቅርብ ርቀት የሚያስተሳስረው የዳባት-አጅሬ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኘውን የመንገድ ግንባታ ለማካሄድ የሚውለው ከ931 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል፡፡  በተጨማሪ


 

በኦሮሚያ ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት የሚገኘው የቆቃ- አዱላላ- ቢሾፍቱ የአስፋልት ኮንክሪትየ መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡

ይህ መንገድ የአዳአ፣ ሊበን ጭቋላ እና የሎሚ ወረዳዎችን የሚያስተሳስር ሲሆን 52 ኪ.ሜ ርዝመት ይሸፍናል፡፡ ለመንገዱ ግንባታ 711.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጠየቀ ሲሆን አጠቃላይ የመንገዱ ወጪ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነው ነው፡፡ የመንገዱ ግንባታ ያካሄደው አሰር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ የተባለ አገር በቀል የሥራ ተቋራጭ በተጨማሪ

 


የአይከል - ዙፋን - አንገረብ የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 140.5 . ርዝመት ያለው ሲሆን ለግንባታው የሚውለው መዋዕለ-ንዋይ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ሆኖ 2.7 ቢሊዮን ብር ወጪ ይደረግበታል፡፡የግንባታ ሂደቱ ለአሠራር አመቺነት በሁለት ኮንትራት የተከፈለ ነው፡፡ በመሆኑም ኮንትራት 1 የአይከል - ዙፋን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ የሚከናወነው በሱር ኮንስትራክሽን ሲሆን የማማከር እና የቁጥጥር ሥራው ሮድ ዲዛይንና ዴቬሎፕመንት ኮንሰልታንትስ እና ጎጎት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ በተባለ ሀገር በቀል አማካሪ ድርጅቶች ነው፡፡በተጨማሪ


በኢትዮጵያ አዘጋጅነት 5 ቀናት ሲደረግ የቆየው 17ኛው የሌበር ቤዝድ ፕራክቲሽነር አህጉራዊ ጉባኤ ቱኒዚያን ቀጣይ አስተናጋጅ አድርጎ በመምረጥ ተጠናቀቀ፡፡

ከአፍሪካ ከኤስያ እና ከአውሮፓ የተለያዩ 27 አገራት የተውጣጡ 450 ተሳታፊዎችና 14 ሚንስትሮችና ተወካዮቻቸው ተሳታፊ የሆኑበት ጉባኤ በዋናነት የሰው ጉልበት ላይ መሰረት ያደረጉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ወጪ ቆጣቢና አዋጭነት ያላቸውን የምህንድና ውጤቶችን በማስተዋወቅ ለወጣቱ ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የሚቻልበትን አማራጮችና እና የዘላቂ ልማት ጎሎችን ለማሳካት መደረግ ስለሚገባቸው አስተዋጽኦዎች በሚሉ

የነቀምት-ቡሬ የአስፋልት መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀመረ።


257 ኪ.ሜ ርዝመት የሚሸፍነው እና በጠጠር ደረጃ የሚገኘው የነቀምት-ቡሬ መንገድ በአስፋልት ደረጃ የግንባታ ስራው በይፋ ተጀመረ ። ይሀው ከ 5.7 ቢልዮን ብር በላይ የሚጠይቀው የመንገድ ፕሮጄክት ወጭ የሚሸፈነው ከአለም ባንክ እና በ ኢትዮጵያ መንግስት ነው። የመንገዱ ግንባታ በ3 አመት የሚ ጠናቀቅ ሲሆን የግንባታ ስራውን በይፋ ያስጀመሩት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ከቡር አቶ ሙክታር ከድር እና የትራንስፖርት ሚንስትሩ ከቡር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ናቸዉ ። የመንገዱን ግንባታ የሚያከናውኑት የውጭ ሀገር የስራ ተቓሪጮች ናቸዉ ። በኮንትራት ውሉ መሰረትም የመንገዱን የዲዛይን ፣የግንባታ እና ለ 5 አመታት ከግንባታ በ ኃላ የጥገና ስራውን የሚያከናውኑ ይሆናል። ይህ አይነቱ የኮንትራት ውል ጥገናን ጭምር ያካተተ በመሆኑ በባለስልጣን መ/ቤቱ ሲተገበር የመጀመሪያው ነው።

Showing 1 - 2 of 7 results.
Items per Page 2
of 4