Top News Top News

የላሊበላ - ኩልመስክ - ሙጃ መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል

የላሊበላ - ኩልመስክ - ሙጃ መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል:: አዲስ አበባ፣ መጋቢት 03፣ 2016 (ኢ መ አ) ፡- የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት መዳረሻ የሆነው የላሊበላ - ኩልመስክ - ሙጃ መንገድ ፕሮጀክት አሁን ላይ በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል።ፕሮጀክቱ 48 ነጥብ 78 ኪሎሜትር የሚሸፍን ኾኖ፣ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ በመንገድ ግንባታው እስከ አሁን የካምፕ ግንባታ፣ የዲዛይን፣ የአፈር ጠረጋ፣ ቆረጣ እና ሙሌት፣ የውኃ ተፋሰስ እንዲሁም የቅድመ-ምርት ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ የግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም በአሁን ወቅት 10 ነጥብ 51 በመቶ ደርሷል፡፡ በተጨማሪም የአነስተኛ እና ከፍተኛ ከልቨርቶች፣ የአስፋልት ንጣፍ እንዲሁም የስድስት ድልድዮች ግንባታ ሥራም በፕሮጀክቱ ተካትቷል፡፡ ... View »

የደብረብርሃን - አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ

የደብረብርሃን - አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናቀቁ :: አዲስ አበባ, የካቲት 4፣ 2016 (ኢመአ) ፡-  የደብረብርሃን - አንኮበር 42 ኪሎሜትር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ሥራዎች የተጠናቀቁ ሲኾን፣ ቀሪ ውስን ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ አሁን ላይ ከግንባታው አጠቃላይ ሥራ 98 በመቶው ተጠናቋል። ከግንባታ ሥራዎች መካከል የ39 ኪሎሜትር የአስፋልት ንጣፍ ፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ፣ ሰብቤዝ ፣ የመንገድ ዳር የአደጋ መከላከያ አጥር እንዲሁም የትራፊክ ጠቋሚ ምልክቶች የማቅለም ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ሀገር በቀሉ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘ ሲሆን ፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ... View »

ዳዬ - ጭሬ - ናንሴቦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ይገኛል

ዳዬ - ጭሬ - ናንሴቦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም  ሂደት ላይ ይገኛል  አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢ መ አ) የሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎችን በቅርበት የሚያስተሳስረው የዳዬ-ጭሬ-ናንሴቦ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አሁናዊ የግንባታ አፈጻጸም 84 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን በቅርቡ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡የመንገድ ግንባታዉ አጠቃላይ 71.4 ኪ.ሜትር ርዛማኔ ያለዉ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 47 ኪ.ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡ አብዛኛዉ የቅድመ አስፋልት ንጣፍ ስራው እየተገባደደ ነው። ቀሪ የአስፋልት ንጣፍ ስራውም በቅርቡ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ ለግንባታው የሚውለው  1,723,608,313 ብር  ሲሆን ይህ... View »

የኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ አፈጻጸም በመስክ ምልከታ ተቃኝቷል።

የኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ  አፈጻጸም በመስክ ምልከታ ተቃኝቷል። የመንገድ ፕሮጀክቱ  በትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ የኢመባ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን  እንዲሁም የባለስልጣኑ  ከፍተኛ  የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው ምስክ ምልከታ የተካሄደው። የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የመንገዱን አሁናዊ እንቅስቃሴ በተመለከቱበት  ውቅት እንዳሉት አካባቢው በግብርና ምርቱ ታዋቂ ቢሆንም ከዚህ ቀደም ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ባለመኖሩ አርሶ አደሩ ከምርቱ መጠቀም ሳይችል እንደቆየ አስታውሰው በቀጣይ መንገዱ ሲጠናቀቅ ምርቱን በፍጥነት ለማዕከላዊ ገበያ እውጥቶ በመሸጥ ተጠቃሚነታቸውን የሚጨምር ነው ብለዋል።... View »

መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን የሊማሊሞ መንገድን የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው።

መልካ ምድራዊ አቀማመጡ አሰቸጋሪ የሆነውን  የሊማሊሞ መንገድን  የሚያቋርጥ አዲስ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ስራው እየተፋጠነ ነው። ፕሮጀክቱ የደባርቅ - ዛሪማ ሊማለሞ ተለዋጭ መንገድ ሲሆን 68.62 ኪ.ሜ ርዝመት አለው፡፡ እስካሁኑ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል የአፈር ጠረጋ ፣ድልዳሎ እና ሙሌት ስራዎች አንዲሁም እስከ 20 ሜትር እርዝመት ያለው የአፈር  የቆረጣ ስራ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም  የሶስት ትልልቅ ድልድዮች ግንባታ ስራ  ፣ የውሃ መፋሰሻ ቱቦዎች እና ቦዮች  ምርት ስራም እየተከናወነ ነው ፡፡ በቀጣዩ አመት የአስፋልት ንጣፍ  ስራ ለመጀመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ  ይገኛል፡፡ የደባርቅ - ዛሪማ ሊማለሞ ተለዋጭ መንገድ ፕሮጀክት ስራን በሚፈለገው... View »
— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 15 results.

what is new? what is new?