Skip to Content
Amharic English

ዜና ዜና

Back

የመካነ ሰላም የከተማ መንገድ ማስፋት ስራ በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 08 ፣ 2017 (ኢመአ)፡- በደቡብ ወሎ  ዞን  2 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው  የመካነ ሰላም ከተማ የመንገድ ማስፋት ስራ በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን  በአሁን ወቅት የፕሮጀክቱ ዓፈጻጸም 80.94 በመቶ ደርሷል።

ይህ የከተማ መንገድ ማስፋት ፕሮጀክት መነሻውን ከኮምቦልቻ-መካነሰላም-ግንደወይን መንገድ ላይ በመካነሰላም ከተማ ውስጥ ከ178+510 በማድረግ እስከ ኪሎ ሜትር 181+487  ድረስ የሚዘልቅ ይሆናል ።

በእስካሁኑ የከተማ መንገድ የማስፋት ስራ  የአስፋልት ንጣፍ፣ አፈር ቆረጣ እና ሙሌት ፣  የድሬኔጅ ስራዎች፣ ሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣ ቤዝ ኮርስ ንጣፍ ፣ እንዲሁም የስትራክቸር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።

ለፕሮጀክቱ ግንባታ   ማስፈጸሚያ  የሚውለውን  ገንዘብ   97,033,590.00 /ዘጠና ሰባት ሚሊየን ሰላሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና  ብር/    የሚሸፈነው  የኢትዮጵያ መንግስት ነው ።

የከተማ ማስፋት ፕሮጀክቱን እያከናወነ  የሚገኘው የኢመአ  የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት  ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ  የኢመአ ኮምቦልቻ መንገድ አውታር ማኔጅመንት ቅ/ጽ/ቤት እያከናወነው  ይገኛል።

የከተማ ማስፋት ፕሮጀክቱን ሲጠናቀቅ ለረጅም ዓመታት የነበረውን የህዝብ ጥያቄ የሚመልስና የከተማዋን እድገት በማፋጠን በከፍተኛ ሚናን ይጫወታል።

ህብረተሰቡንም ሆነ የመስመሩን ተጠቃሚዎች ከትራፊክ አደጋ የጸዳ እና በተሻለ ሁኔታ የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል።

ከቦረና ፣ ሳይንት አጅባር፣ ደንሳ፣ ከላላና ለጋምቦ ወረዳዎችን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ለመጓዝ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የመካነሰላም ከተማ አቋርጠው የሚያልፉ ከመሆናቸው አንጻር ይህ መንገድ በአስፋልት ኮንክሪት መገንባቱ ጠቀሚታው ከፍ ያል ነው ።

የመካነ ሰላም የከተማ መንገድ ማስፋት ፕሮጀክቱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ  የጎን ስፋት ትከሻን ጨምሮ  በከተማ 20.5 ሜትር እና 1.5ሜትር አካፋይ እንዲኖረው ተደርጎ እየተሰራ ነው።

በተጨማሪም
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads


World Quality Day World Quality Day

Web Content Display Web Content Display

የስራ ሂደት የስራ ሂደት

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

ተነቀሳቃሽ ምስል ተነቀሳቃሽ ምስል

FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 6 results.

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP

የህትመት ዉጤቶች የህትመት ዉጤቶች