Media Gallery








NEWS
የአዲስ - ጊቤ ከባድ ጥገና ፕሮጀክት በተሻለ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኢ መ አ):- የአዲስ አበባ - ጅማ ዋና መንገድ አካል የኾነው የአዲስ-ጊቤ አስፋልት መንገድ ከባድ ጥገና ፕሮጀክት በተሻለ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። መንገዱ ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግድ በመሆኑና በአገልግሎት ብዛት በመጎዳቱ ምክንያት ነው ከባድ ጥገና እየተደረገለት የሚገኘው። ከዚህም ባሻገር የወጪ ንግድም መተላለፊያ በመኾኑ የመስመሩን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት በሚመጥን መልኩ መልሶ ግንባታ እየተደረገለት ነው። የከባድ ጥገና ፕሮጀክቱ ለግንባታ አመቺነት ሲባል በሁለት ክፍሎች ተከፋፍሎ እየተከናወነ ይገኛል። ለጥገናው በድምሩ 3 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲኾን፥ ሙሉ ወጪው በፌደራል መንግስት ይሸፈናል። በክፍል - 2 የአዲስ -ጊቤ ወንዝ የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት 64 ኪሎሜትር የሚሸፍን ኾኖ፥ መነሻውን... Read More »
የሀሚድ ድልድይ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2017 (ኢ መ አ):- የወልዲያ - ሮቢት መንገድ ክፍል የኾነው የሀሚድ ወንዝ የብረት ድልድይ ጥገናው መጠናቀቁን ተከትሎ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ተደርጓል። ድልድዩ ከዚህ ቀደም ከተፈቀደው ክብደት በላይ በጫነ ከባድ ተሽከርካሪ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር ይታወቃል። በወቅቱ ተለዋጭ መንገድ በማዘጋጀት ተሽከርካሪዎች እንዲገለገሉ ማድረግ ተችሏል። የብረት ድልድዩን መልሶ ለመገንባትም በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት እንዲሁም የድልድይ እና ስትራክቸር ዳይሬክቶሬት ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ድልድዩን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመጠገን ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክፍት ማድረግ ተችሏል። 45 ነጥብ 7 ሜትር ርዝመት ያለው ይኸው ድልድዩ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ክፍት ተደርጎ አገልግሎት እየሰጠ... Read More »
የባቱ - አርሲነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ 84 ነጥብ 50 በመቶ ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኢ መ አ):- የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ-ሐዋሳ ኮንትራት 3 ፡ ባቱ - አርሲነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ 84 ነጥብ 50 በመቶ ደርሷል፡፡ 57 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የመንገዱ ግንባታ የእስካሁን ሂደትም የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት ፣ የውሃ መፋሰሻ ቦዮች (Side Ditches) ፣ የሰብ ቤዝ እና ቤዝ ኮርስ ፣ ሚዛን ጣቢያዎች እና ዞሮ መመለሻ መንገዶች ፣ የስትራክቸር ፣ የመኪና መሸጋገሪያ ፣ የእግረኛ/የእንስሳት መሸጋገሪያ ፣ የወንዝ ድልድዮች ፣ የመንገድ ዳር አጥር ፖሎች የማምረት ፣ የ Intelligent Transport System (ITS) ቱቦ ቀበራ ፣ የአስፋልት ማንጠፍ እንዲሁም በዋናው መንገድ እና አገናኝ መንገዶች ላይ ሌሎች የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ... Read More »
የሙስሊ - ኮሪ - ቴሩ ምዕራፍ አንድ የመንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ እየተከናወነለት ነው
ሰመራ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኢ መ አ):- በአፋር ክልል የሙስሊ - ኮሪ - ቴሩ መንገድ ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ ከኪሎሜትር 00 እስከ ኪሎሜትር 84 ያለው የአስፋልት ንጣፍ እየተከናወነለት ነው። የመንገድ ግንባታው 84 ነጥብ 2 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ በአፋር ክልል አውሲረሱ እና ፋንቲረሱ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ሁለት ወረዳዎችን እና በርካታ ቀበሌዎችን ያስተሳስራል። አሁን ላይ የ20 በመቶ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ፣ የ21 በመቶ የስትራክቸር፣ የ98 በመቶ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የ34 በመቶ ሰብቤዝ እንዲሁም የ10 በመቶ የአስፋልት ንጣፍ ሥራዎች ተከናውነዋል። የሰባት ድልድዮች ግንባታም በፕሮጀክቱ ተካትቷል። በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 56 በመቶ ደርሷል። የተመዘገበውን አበረታች አፈጻጸም አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት... Read More »
የመንገድ ዘርፍ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አካሄዶች ላይ ውይይት ተካሄደ
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የኢ መ አ መንገድ ምርምር ማዕከልን ጎብኝተዋል አዲስአበባ፣ መጋቢት 09፣ 2017 (ኢ መ አ):- የመንገድ ዘርፍ አፈጻጸም ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አካሄዶች ላይ በኢ መ አ የመንገድ ምርምር ማዕከል ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ በመንገድ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ዘርፉን የገጠሙት ተግዳሮቶች እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ገለጻ ተደርጓል። በተጨማሪም ከሚንስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ ሊደረግባቸው የሚችሉ ጉዳዮችም ተለይተው ቀርበዋል። በዚህም ረገድ የሀገሪቷን የመንገድ ሽፍን የመንገድ ዘርፍ ልማት ፕሮግራሙ በ1989 ከነበረበት 23 ሺህ ኪሎሜትር አሁን ላይ ወደ 171 ሺህ ማድረስ እንደተቻለ ገላጻው ላይ ተጠቁሟል። ሆኖም ባለፉት ጊዜያት የጋጠሙ... Read More »
ERA GIS PORTAL
20TH REGIONAL CONFERNCE
URGENT NOTICE
CALL FOR Workshop

Manuals And Standard Document
FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY
-
Six Month Accomplishment
-
ERA 2013 Approved Capital Budget
-
ERA 2013 Approved Capital Budget
-
ERA 2013 Approved Capital Budget
-
2013 Six Month Money Usage
— 5 Items per Page