Media Gallery
NEWS
የጋሸና-ቢልባላ-ሰቆጣ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኘው የኮንትራት 1 የጋሸና - ቢልባላ እና የኮንትራት 2 ፡ የቢልባላ - ሰቆጣ የአስፋልት ኮንክሪት ቀሪ ሥራዎችን የማጠናቀቂያ ፕሮጀክት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መሐመድ አብዱራህማን ፣ የክልሉ የዞን እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አረጋ ከበደ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአካባቢዉ ማህበረሰብ በእዉቀቱ፣ በባህሉ እና ባለዉ የተፈጥሮ ሀብት ለሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገ ነዉ። በመሆኑም አካባቢው ባለዉ ሀብት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብሎም ለሀገር ልማት በተገቢዉ መልኩ ለማዋል ዛሬ በይፋ ያስጀመርነዉ መንገድ ጠቀሜታዉ ከፍ ያለ ነዉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን በበኩላቸው መንገዶቹ ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ፋይዳ አንጻር ተጠናቀው ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ይችሉ ዘንድ ፕሮጀክቱን ለማስጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው ግንባታው በዛሬው ዕለት በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል።
የፕሮጀክቶቹን ከፍተኛ ጠቀሜታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በተገቢው የጊዜና የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
የኮንትራት 1 እና 2 ፕሮጀክት በአጠቃላይ 204.8 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚሸፍን ነው።
በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወን የተቻለ ሲሆን ፣በቀጣይም ያልተጠናቀቁ ስራዎች ማለትም የውሃ ማፋሰሻ ትቦዎች ፣ የሰቤዝ ፣ የቤስኮርስ እና የአስፋልት ስራዎችን በአፋጣኝ ለማጠናቀቅም እየተሰራ ይገኛል፡፡
የመንገዱን ግንባታ የአማራ ክልላዊ ብሄራዊ መንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ህብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ያከናውናሉ።
የኮንትራት 1 ፕሮጀክትን የማማከርና ቁጥጥሩን ሥራ ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድር ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚያካሂድ ሲሆን በተመሳሳይ የኮንትራት 2 ደግሞ ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ኃ/የ/የግ/ማህበር ከቤዛ ኢንጂነሪንግ ኬኒያ ሊሚትድ ጋር በጣምራ ያካሂዱታል፡፡
ለግንባታው የሚውለው 5,119,831,284 ( አምስት ቢሊዮን አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ብር የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ የላሊበላ ከተማን ፣ የላስታ ፣ የመቄትን እና የዋድላ ወረዳዎች እንዲሁም ፣ በዋግህምራ ብሄረሰብ ዞን ጋዝጊብላና ሰቆጣ ወረዳን የሚያገናኝ ነው፡፡
በተጨማሪም በዓለም የቅርስ መዝገብ (UNESCO) ተመዝግቦ የሚገኘውና ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ያለበት የላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያኖች እና የተለያዩ አብያተ መዛግብት የሚገኙት በዚሁ የመንገድ ኮሪደር ውስጥ መሆኑ የመንገዱን አስፈላጊነት ከፍ ያደርገዋል፡፡
በተጨማሪም
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
World Quality Day
Web Content Display
ERA GIS PORTAL
URGENT NOTICE
CALL FOR Workshop
Manuals And Standard Document
FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY
-
Six Month Accomplishment -
ERA 2013 Approved Capital Budget -
ERA 2013 Approved Capital Budget -
ERA 2013 Approved Capital Budget -
2013 Six Month Money Usage
