Media Gallery
NEWS
የደብረብርሃን - ደነባ - ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር - ደነባ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን ፕሮጀክት በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው 108.25 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ከደብረ ብርሃን - ደነባ - ለሚ መገንጠያ እና ከደነባ - እነዋሪ - ጅሁር እየተገነባ የሚገኘው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የአስፋልት ማልበስ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ።
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት መነሻውን ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ በማድረግ ለሚ መገንጠያ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን እንዲሁም ከጅሁር ከተማ በመነሳት መዳረሻውን ደነባ ከተማ ላይ ያደርጋል።
በእስካሁኑ የመንገድ ግንባታ ስራ የአስፋልት ንጣፍ፣ አፈር ቆረጣ እና ሙሌት ፣ የድሬኔጅ ስራዎች፣ ሰብ ቤዝ ንጣፍ ፣ ቤዝ ኮርስ ንጣፍ ፣ እንዲሁም የስትራክቸር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል።
ለግንባታ ማስፈጸሚያ የሚውለውን ገንዘብ 3,613,766,908.69 (ሶስት ቢሊዮን ስድስት መቶ አስራ ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስምንት ብር ከ ስልሳ ዘጠኝ ሣንቲም) ብር የሚሸፈ ነው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱን እያከናወነ የሚገኘው አገር በቀሉ ሰንሻይን የስራ ተቋራጭ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ኤቢኤም ኢንጂነርስ እና ንዑስ ኮንሰልታት ፕላስ ኮንሰልት ሃ/የተ/የግ/ማህበር በጋራ እያከናወኑ ይገኛሉ።
የመንገድ የግንባታ ፕሮጀክቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለአካባቢዉ ህብረተሰብም ሆነ ለመስመሩ ተጠቃሚዎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥን በማምጣት ደረጃ ከፍተኛ የሆነ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
በለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሚመረተውን ሲሚንቶ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ የግንባታ ኢንዱስትሪውን እድገት ከማፋጠኑም ባሻገር የዋጋ ግሽበትን ያረጋጋል።
በአካባቢው የሚገኙት አርሶ አደሩ ምርቱን ወደ ገበያ ለማውጣት እና የኢንዱስትሪ ውጤቶችንም ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ ተደራሽ በማድረግ የገበያ ማረጋጋት ስራ ማከናወን ያስችላል።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ የጎን ስፋት ትከሻን ጨምሮ በዞን ከ25.5 - 32.1 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር፣ በወረዳ 19.45 ሜትር ሲሆን በገጠር 11 ሜትር ነው።
በተጨማሪም
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
World Quality Day
Web Content Display
ERA GIS PORTAL
URGENT NOTICE
CALL FOR Workshop
Manuals And Standard Document
FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY
-
Six Month Accomplishment -
ERA 2013 Approved Capital Budget -
ERA 2013 Approved Capital Budget -
ERA 2013 Approved Capital Budget -
2013 Six Month Money Usage
