Vacancy Announcement Vacancy Announcement

Title Author Categories Publish Date Expiration Date View Count
External vacancy Feb 11 2026 Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 2/11/26 112
External Vacancy January 22 2026 Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 1/22/26 517
Exam Result For Junior Engineer Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 1/28/25 3119
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 1291
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 967
Junior Printing And Laminating Officer Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 899
Law Expert Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 1079
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 858
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 1043

Top News Top News

Back

የድሬዳዋ - ሽንሌ እና የድሬዳዋ ከተማ ተለዋጭ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም 84 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 04 ፣ 2017 (ኢ መ አ)፡- የድሬዳዋ  ከተማን  ከሽንሌ  ከተማ  ጋር  የሚያገናኘው  የድሬዳዋ - ሽንሌ  እና የድሬዳዋ  ከተማ  ተለዋጭ  የአስፋልት  ኮንክሪት  መንገድ  ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም 84 በመቶ ደርሷል፡፡

29  ነጥብ  29  ኪሎ ሜትር በሚረዝመው  መንገድ አሁን ላይ  የአፈር ቆረጣ  እና ሙሌት ፣ የድሬኔጅ ፣ የቤዝ ኮርስ እና የአስፋልት  ንጣፍ  እንዲሁም  የስትራክቸር  ሥራዎች  በመከናወን  ላይ  ይገኛሉ፡፡

በፕሮጀክቱ  የሥራ  ሂደት ወቅት ከፍተኛ  የሆነ የወሰን  ማስከበር ችግር  ይስተዋል የነበረ ሲሆን ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች ችግሩ እንዲፈታ በመደረጉ  ግንባታው  በእቅዱ  መሰረት  እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ዓለም -አቀፉ ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ  ኮንስትራክሽን  ኮርፖሬሽን   የመንገዱን  ግንባታ  እያከናወነ  የሚገኝ  ሲሆን  ቤዛ ኢንጂነሪንግ  ኬንያ ሊሚትድ የፕሮጀክቱን የማማከር እና የቁጥጥር  ሥራ እየሰራው ነው፡፡

ፕሮጀክቱን ለማካሄድ አገልግሎት ላይ የሚውለው 1,146,143,392 ( አንድ  ቢሊዮን  አንድ  መቶ አርባ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ ሶስት  ሺህ  ሶስት  መቶ  ዘጠና ሁለት ብር በኢትዮጵያ  መንግስት  የተሸፈነ ነው፡፡

መንገዱ  በወረዳ  21.5 ሜት ር ፣ በከተማ 25 ሜትር እንዲሁም  በገጠር  7  ሜትር አጠቃላይ የጎን ስፋት  እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ  ይገኛል፡፡

የመንገዱ  መገንባት የድሬዳዋ እና  የሽንሌ ከተሞችን  የሚያገኛን ከመሆኑም ባሻገር ከጂቡቲ  በድሬዳዋ ደወሌ  መንገድ በኩል  የሚመጡ የጭነት ተሸከርካሪዎች  የድሬደዋ ከተማን  ሳይነኩ  እንዲያልፉ  በማድረግ   በከተማው  ውስጥ ሊፈጠር ሚችለውን የትራፊክ መጨናነቅ  ያስቀራል፡፡

በተጨማሪም  በአካባቢው  በስፋት  የሚመረቱ  የግብርና  ምርቶችን   በቀላሉ   ወደ ገበያ  በማውጣት  የገበያ ትስስርን ለመፍጠር ያስችላል፡፡

በተጨማሪም
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads