Vacancy Announcement Vacancy Announcement

Title Author Categories Publish Date Expiration Date View Count
External vacancy Feb 11 2026 Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 2/11/26 112
External Vacancy January 22 2026 Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 1/22/26 518
Exam Result For Junior Engineer Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 1/28/25 3120
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 1291
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 967
Junior Printing And Laminating Officer Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 899
Law Expert Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 1080
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 859
Office manager Ethiopian Roads Administration gov ERA: Vacancy 11/5/20 1044

Top News Top News

Back

20ኛው የዓለም የስራ ድርጅት የሌበር ቤዝድ ፕራክቲሽነርስ አህጉራዊ ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው


 
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ኢመአ)፡ 20ኛው የዓለም የስራ ድርጅት የሌበር ቤዝድ ፕራክቲሽነርስ አህጉራዊ ኮንፈረንስ ከግንቦት 11 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ፣የአለም ሥራ ድርጅትና የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቁ።

 ይህን አህጉራዊ ኮንፈረንስ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከአለም የሥራ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው የሚያዘጋጁት፡፡
 
ኮንፈረንሱን አስመልክቶ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው " የማይበገር ማህበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ ፡ የሰው ሃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢቨስትመንት አካሄዶች የሚል መሪ ሃሳብ አንግቧል ፡፡ ይህም የዘላቂ ልማትን አስፈላጊነት የሚያንጸባርቅ እንዲሁም ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ፕሮግራሞች ኢኮኖሚያዊ እድገትን ብቻ ሳይሆን የአካባቢ ጥበቃን ፣ የማህበረሰብ ደህንነትን ፣ አካታችነትን እና ዘላቂ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ እንደሚገባ አጉልቶ የሚያሳይ ነው ፡፡
 
በዚህ ኮንፈረንስ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ሚኒስትሮች ፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች ፣ የሲቪክ እና መንግታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ፣ የአሰሪዎች እና የሰራተኞች ፌደሬሽኖች ተወካዮች እንዲሁም የዘርፉ ምሁራንና ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን በአጠቃላይ አገራችንን ጨምሮ ከአምስት አህጉራትና ከሃምሳ በላይ አገራት ፣ ከ1500 በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ ፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ የዘርፉ ተመራማሪዎች ፣ ፖሊሲ አውጪዎች ፣ እና ባለሙያዎች በሳል የጥናትና ምርምር ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ፡፡ ከግንቦት 11 እሰከ 15 ቀን ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊካሄድ የታቀደው 20ኛው የአለም ስራ ድርጅት የሌበር ቤዝድ ፕራክቲሽነርስ አህጉራ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ እንደተለመደው እንግዳ ተቀባይነቷን ከምርም የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲናና የኮንፈረንስ ማእከል መሆኗን የምታሳይበት እንዲሁም በዓለም አቀፍ መድረክ እንድትደምቅ ሌላ እድል የሚፈጥር ነው ፡፡

በተጨማሪም
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads