Skip to Content
Amharic English

NEWS NEWS

በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ መከናወኑ ተገለጠ

  አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26 ቀ ን 2018 ዓ.ም (ኢመአ)፦ በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ እና 12 ሺህ 882 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የተለያዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ። ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ በዓለምገና ኢንጅነሪንግ እና ማኔጅመንት ማሠልጠኛ ማዕከል ከአመራሮችና ከሠራተኞች ጋር አጠቃላይ ዓመታዊ የውይይት መድረክ አካሂዷል።   በተቋሙ ፕላንግና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በቀረበው ሪፖርት መሠረት፤ በበጀት ዓመቱ የ238 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም የ16 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ማጠናከር ሥራዎች በስኬት ተከናውነዋል። ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የምህንድስና ግዢ፣ የዲዛይን ፕሮጀክቶች እንዲሁም የተቋማዊ አቅም ግንባታ... Read More About በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ መከናወኑ ተገለጠ »

የጎንጂ-ቆለላ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት 98.82 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢመአ) ፤ በጎንጂ ቆለላ ወረዳ የሚገነባው የቆሬ - አዲስ ዓለም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የ10.59 ኪሎ ሜትር ግንባታን በማጠናቀቅ 98.82 በመቶ አጠቃላይ አፈጻጸም ላይ ደርሷል ። ከባህር ዳር ወደ ሞጣ በሚወስደው መንገድ ላይ ከምትገኘው ቆሬ ቀበሌ ተነስቶ ምስራቅ አቅጣጫ በመጓዝ ሂዳሴ መንደርን አቋርጦ አዲስ ዓለም ከተማ የሚገባው ይህ ፕሮጀክት፣ በአጠቃላይ 10.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ቀድሞ የነበረውን የጠጠር መንገድ ወደ አስፋልት ደረጃ የሚያሳድገው ይህ ግንባታ፣ የመንገዱ ስፋት በገጠር 10 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በወረዳ 21.5 ሜትር ሆኖ እየተገነባ ይገኛል።   ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሲሆን በአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ... Read More About የጎንጂ-ቆለላ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት 98.82 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደረሰ »

9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም(ኢመአ): የመንገድ ልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሳይንሳዊ ምርምርና በቴክኖሎጂ ለማገዝ የተዘጋጀው 9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን፣ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሂሩት ዮሐንስ እና የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደገብርኤልን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል። ባለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄዱት ተከታታይ የምርምር ኮንፈረንሶች በሀገሪቱ የመንገድ ልማት ላይ ውጤታማ ለውጦችን ማምጣት ችለዋል። በአሁኑ 9ኛ ኮንፈረንስም በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፣ ተያያዥ አውደርዕይም ተካሂዷል።... Read More About 9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሄደ »

የጣርማበር - መለያያ ሰፌድ ሜዳ የጠጠር መንገድ ጥገና እየተካሄደለት ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21/2018 (ኢመአ)፦ ከጣርማበር መለያያ እስከ ሰፌድ ሜዳ ለሚዘልቀው የጠጠር መንገድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል። ጥገናው የሕዝቡን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል ታስቦ በትኩረት እየተከናወነ ያለ ሥራ ነው። ይህ አጠቃላይ 118 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፣ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት ግንባታው ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሳይጠናቀቅ ተስተጓጉሎ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ግን ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ በሆነው 21.6 ኪሎ ሜትር የመንገዱ ክፍል ላይ ሰፊ የጥገና ሥራ እየተሠራ ይገኛል። እስካሁንም በማሽን የቦይ ማጽዳት፣ የድንጋይ ሙሌት፣ በጭቃ የተበላሹ አካባቢዎችን የማስወገድ እንዲሁም በግሬደር የመንገዱን አካል የማስተካከልና የማጠናከር ሥራዎች ተከናውነዋል። የጥገና... Read More About የጣርማበር - መለያያ ሰፌድ ሜዳ የጠጠር መንገድ ጥገና እየተካሄደለት ነው »

የሶዶ መንገድ አውታር አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት  1,890 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና አከናወነ፤ አፈጻጸሙም 96.3% ሆኖ ተመዝግቧል

ሶዶ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም(ኢመአ): በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ስር የሚገኘው የሶዶ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያቀዳቸውን የፊዚካልና የፋይናንሻል የሥራ ግቦች በስኬት አጠናቀቀ። ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 1.81 ቢሊዮን ብር በጀት መድቦ የነበረ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1.56 ቢሊዮን ብሩን (86.18%) ለተለያዩ የጥገናና መሰረተ ልማት ሥራዎች ማዋል ችሏል። በፊዚካል አፈጻጸም ረገድም ከተቀመጠው 1,963 ኪሎ ሜትር የጥገና ዕቅድ ውስጥ 1,890 ኪሎ ሜትር በማጠናቀቅ  96.3% አፈጻጸም አስመዝግቧል። ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 3,242.5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ሽፋን ያስተዳድረል፡፡ ከዚህም ውስጥ 68 በመቶው (2,196.5 ኪ.ሜ) የአስፋልት ኮንክሪት ሽፋን... Read More About የሶዶ መንገድ አውታር አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት  1,890 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና አከናወነ፤ አፈጻጸሙም 96.3% ሆኖ ተመዝግቧል »

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP

Call For Conference Call For Conference

ERA GIS PORTAL ERA GIS PORTAL

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

  • Ads

Web Content Display Web Content Display