Skip to Content
Amharic English

NEWS NEWS

Back

የኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ አፈጻጸም በመስክ ምልከታ ተቃኝቷል።

የኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ  አፈጻጸም በመስክ ምልከታ ተቃኝቷል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ  በትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣ የኢመባ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን  እንዲሁም የባለስልጣኑ  ከፍተኛ  የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው ምስክ ምልከታ የተካሄደው። የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የመንገዱን አሁናዊ እንቅስቃሴ በተመለከቱበት  ውቅት እንዳሉት አካባቢው በግብርና ምርቱ ታዋቂ ቢሆንም ከዚህ ቀደም ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ባለመኖሩ አርሶ አደሩ ከምርቱ መጠቀም ሳይችል እንደቆየ አስታውሰው በቀጣይ መንገዱ ሲጠናቀቅ ምርቱን በፍጥነት ለማዕከላዊ ገበያ እውጥቶ በመሸጥ ተጠቃሚነታቸውን የሚጨምር ነው ብለዋል።

አቶ ካሳሁን ጎፌ ጨምረውም የኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ ተጠናቆ ተገቢውን ግልጋሎት መስጠት እንዲችል ካስፈለገ    ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ በተለይም ኢትያ፣ ሁሩታ፣ ዲክሲስ እና ሮቤ ከተሞች ላይ ያጋጠመውን ዩቲሊቲ ተቋማት በሆኑት መብራት ፣ ቴሌ እና የመጠጥ ውሀ መስመሮች እንዲሁም  የመኖሪያ ቤቶች  በፍጥነት ከመንገድ ክልል አለመነሳት ጋር ተዳምሮ የሚስተዋሉ  ችግሮችን በአስቸኳይ ሊቀረፉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

 የኢመባ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን  በበኩላቸው 75.6 ኪሜ የሚረዝመው የኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከዚህ ቀድም በተቋራጩ አቅም ማነስ ምክንያት በመጓተቱ የቅሬታ ምንጭ  የፈጠረ ቢሆንም የባለስልጣኑ መ/ቤት  ከተቋራጩ ጋር በገባው ውል መሰረት ግንባታውን እንዲያፋጥን ከጋራ መግባባት ላይ መድረስ በመቻሉ  ነው የመንገድ ግንባታ እንቅስቃሴው ዳግም ሊነቃቃ የችለው ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ለፕሮጀክቱ በስኬት መጠናቀቅ  የባለድርሻ አካላት ትብብር እና ድጋፍ ከምንም በላይ ወሳኝ እንደሆነ ገልጸው የባለስልጣኑ መ/ቤትም ጥብቅ ክትትል ያደርግልም ብለዋል  ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን ።ኢተያ – ሮቤ ምእራፍ አንድ ምንገድን በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታውን  የሚያከናውነው የስራ ተቋራጭ ቻይና ሬል ዌይ ቁጥር 3 የተባለው አለም አቀፉ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው ፡፡ለመንገዱ ግንባታ ስራ የሚውለውን 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

በእስካሁኑ 15 ኪሜ የሚሸፍን የአስፋልት ንጣፍ ስራን ጨምሮ ን የአፈር ቆረጣና ሙሌት እንዲሁም የውሃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራ ስራም በመካሄድ ላይ ሲሆን በቀጣይ አመት ዋና ዋና የመንገድ ግንባታ ስራዎችን በማጠናቀቅ ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ ይጠበቃል። ከአስፋልት ንጣፍ ስራው ጎን ለጎበቀጣይ የ6  ድልድዮች ግንባታ ስራን ጨምሮ የስትራክቸርና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛል። የኢተያ ሮቤ መንገድ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ ሆኖ ለትራንስፖርት በእጅጉ አሰቸጋሪ የነበረ ነው ፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅም በአካባቢው የሚመረቱ ከፍተኛ የግብርና ምርት ውጤቶችንና የቁም እንስሳትን በቀጥታ ወደ ማእከላዊ ገበያ በፍጥነት በማድረስ አምራች ሸማቹን ተጠቃሚ ያደርጋል። በመንገዱ ብልሽት ሳቢያ በተለይም በክረምት ወቅት የሚከሰተውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መስተጓጎል በማስቀረት ምቹ የትራንስፖርት ፍሰትን ይፈጥራል ፡፡ የኢተያ – ሮቤ የመንገድ ግንባታ ኘሮጀክት የስራውን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር እየተሳተፈ የሚገኘው አገር በቀሉ ሃይ ዌይ ኢንጅነርስ ኤንድ ኮንሰልታንትስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ድርጅት ነው ፡፡


የመስክ ስራ ቅኝቱ  ከኢተያ ሮቤ ፕሮጀክት በመቀጠል 92.6 ኪ.ሜ የሚረዝመው የአርሲነገሌ _ቢላሎ - ቀርሳ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራ እንቅስቃሴ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት  እንዲሁ ምልከታ ተደርጓል። በዚህም  የፕሮጀክቱን አፈጻጸም አሁን ካለበት በበለጠ ማሳካት እንዲቻል የሁሉም አካላት ትብብር ውሳኝ መሆኑ ተነስቷል።


20TH REGIONAL CONFERNCE 20TH REGIONAL CONFERNCE

CALL FOR Workshop CALL FOR Workshop

FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY FINANCIAL TRANSPARENCY & ACOUNTABLITY

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP