Media Gallery
NEWS
በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ መከናወኑ ተገለጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26 ቀ
ን 2018 ዓ.ም (ኢመአ)፦ በ2018 በጀት ዓመት የ580 ኪሎ ሜትር አዳዲስ መንገዶች ግንባታ እና 12 ሺህ 882 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የተለያዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ። ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ በዓለምገና ኢንጅነሪንግ እና ማኔጅመንት ማሠልጠኛ ማዕከል ከአመራሮችና ከሠራተኞች ጋር አጠቃላይ ዓመታዊ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በተቋሙ ፕላንግና ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በቀረበው ሪፖርት መሠረት፤ በበጀት ዓመቱ የ238 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም የ16 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ማጠናከር ሥራዎች በስኬት ተከናውነዋል። ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የምህንድስና ግዢ፣ የዲዛይን ፕሮጀክቶች እንዲሁም የተቋማዊ አቅም ግንባታ ተግባራትን ማከናወኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 24 የመንገድ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የኢተያ - አርሲ ሮቤ፣ የእስቴ - ስማዳ፣ የድሬዳዋ ባይፓስና ሽንሌ፣ የጅግጅጋ ከተማ ማለፊያ (ባይፓስ) መንገድ እንዲሁም የሳውላ - ቃቆ መንገድ ፕሮጀክቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ተቋሙ በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት ከ1 ሺህ 67 ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶችን ለመገንባት እና ከ16 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የተለያዩ መንገዶችን ለመጠገን አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱ ተመላክቷል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር መሐመድ አብዱራህማን (ኢንጅነር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት፤ የ2018 በጀት ዓመት ተቋሙ የተመሠረተበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ያከበረበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ መሆኑን አስታውሰዋል። ተቋሙ ባለፉት 75 ዓመታት ሰፊ የመንገድ መሠረተ-ልማት አውታሮችን በመዘርጋት ኢትዮጵያን እርስ በርስ ማስተሳሰር የቻለና ለአገሪቱ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የማይተካ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ በ2019 በጀት ዓመት በመንገድ ዘርፉ የተጣሉትን አገራዊ ግቦች በውጤታማነት ለማሳካት የተጀመረው ተቋማዊ ሪፎርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የአሠራር ሽግግሮችንና የዲጂታላይዜሽን በአግባቡ ከመተግበር ጎን ለጎን የሥራ ባህልንና የበጀት አጠቃቀምን በተጠያቂነትና በግልጽነት መንፈስ መምራት እንደሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል communication@era.gov.et
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
FIND US ON GOOGLE MAP
Call For Conference
