Skip to Content
Amharic English

NEWS NEWS

የሚኤሶ - ሒርና መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ነው

የሚኤሶ - ሒርና መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ነው አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27/2019 (ኢመአ)፦ የኢትዮ-ጅቡቲ ትራንስፖርት ኮሪደር አካል ለሆነው የሚኤሶ - ሒርና 69 ኪሎ ሜትር መንገድ፣ የመስመሩን ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት በብቃት ማስተናገድ እንዲያስችል የከባድ ጥገና ሥራ እየተከናወነለት ይገኛል።  ይህ የትራንስፖርት መስመር የወጪና ገቢ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚከናወንበት እና የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች በብዛት የሚመላለሱበት በመሆኑ፣ ከቀላል እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚደርስ ጉዳት አስተናግዶ ቆይቷል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የተጀመረውን የከባድ ጥገና ፕሮጀክት ሀገር በቀሉ "ዮንአብ ኮንስትራክሽን" እያከናወነው ሲሆን፣ የጥራት ቁጥጥርና የማማከር ሥራውን ደግሞ "ሃይዌይ ኢንጅነርስ ኤንድ ኮንሰልታንትስ" በመሥራት ላይ ይገኛል።   ... Read More About የሚኤሶ - ሒርና መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ነው »

የባሕር ዳር ዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ ሥራ 95 በመቶ ተጠናቀቀ

የባሕር ዳር  ዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ ሥራ 95 በመቶ ተጠናቀቀ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24/2019 (ኢ መ አ):- በሀገራችን በዓይነቱ እና በዘመናዊነቱ የመጀመሪያ የኾነው የአዲሱ የባሕር ዳር ዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ ሥራ 95 በመቶው የተጠናቀቀ ሲኾን፥ ቀሪ ውስን ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ ነው።   ዋናው የመዳረሻ መንገድ መነሻውን ከሄኒ ጋርደን መገንጠያ አድርጎ እስከ ዘንዘልማ ጎንደር መውጫ ድረስ የሚዘልቅ ሲኾን፥ በአጠቃላይ 4 ነጥብ 72 ኪሎ ሜትር ይረዝማል። መንገዱ የአውቶቡስ እና የታክሲ መቆሚያዎችን ጨምሮ 59 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲኾን፥ በግራና በቀኝ 3 ተሽከርካሪዎችን በተመሳሳይ ጊዜ (በአጠቃላይ 6 ተሽከርካሪዎችን) የማስተናገድ አቅም አለው።... Read More About የባሕር ዳር ዓባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ ሥራ 95 በመቶ ተጠናቀቀ »

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ተከበረ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ተከበረ ዓለምገና፣ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢመአ)፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተመሠረተበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት እና የመንገድ አውታር የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በዓለምገና ከተማ በድምቀት አከበረ።   በክብረ በዓሉ ላይ የዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ተመስገን አለማየሁ ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለሀገራችን ብዙ ውለታ የዋለ ታላቅ ተቋም መሆኑን ገለጹ። የሚመሩት ዲስትሪክትም ሀገሪቱን በመንገድ ኔትዎርክ ለማስተሳሰር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን አብራሩ። አክለውም ዲስትሪክቱ... Read More About የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በዓለምገና መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ተከበረ »

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ የመንገዶች ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ እና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተቋሙን 75ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል በጋራ አከበሩ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ የመንገዶች ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ እና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተቋሙን 75ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል በጋራ አከበሩ ድሬዳዋ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢመአ)፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተመሰረተበት 75ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል በድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ በመንገድ አውታር (ኔትወርክ) አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እና በፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤቶች በጋራ አዘጋጅነት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ። በጋራ በተሰናዳው በዚህ ታሪካዊ የክብረ-በዓል መድረክ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲስትሪክቱ ሠራተኞች፣ የድሬዳዋ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ የድሬዳዋ፣ የጅግጅጋ እና የጎዴ... Read More About የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ የመንገዶች ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ እና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተቋሙን 75ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል በጋራ አከበሩ »

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የወላይታ ሶዶ መንገድ ዲስትሪክት፣ መንገድ ኔት ወርክና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ት ቤት የኢመአን የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል አከበሩ

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የወላይታ ሶዶ መንገድ ዲስትሪክት፣ መንገድ ኔት ወርክና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ት ቤት የኢመአን የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል አከበሩ ወላይታ ሶዶ፣ ጥቅምት 11 ቀን 2019 (ኢመአ)፡የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተመሠረተበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል የወላይታ ሶዶ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ እና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት በጋራ በመሆን በድምቀት አክብረዋል። በበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መንግሥቱ ትግሮ እንዲሁም የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ይልማ ሃይለማርያምን ጨምሮ ከተለያዩ ዞኖች የተጋበዙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክብር... Read More About የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የወላይታ ሶዶ መንገድ ዲስትሪክት፣ መንገድ ኔት ወርክና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ት ቤት የኢመአን የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል አከበሩ »

FIND US ON GOOGLE MAP FIND US ON GOOGLE MAP

Call For Conference Call For Conference

ERA GIS PORTAL ERA GIS PORTAL

URGENT NOTICE URGENT NOTICE

  • Ads

Web Content Display Web Content Display