Media Gallery
NEWS
የጎንጂ-ቆለላ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት 98.82 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢመአ) ፤ በጎንጂ ቆለላ ወረዳ የሚገነባው የቆሬ - አዲስ ዓለም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የ10.59 ኪሎ ሜትር ግንባታን በማጠናቀቅ 98.82 በመቶ አጠቃላይ አፈጻጸም ላይ ደርሷል ። ከባህር ዳር ወደ ሞጣ በሚወስደው መንገድ ላይ ከምትገኘው ቆሬ ቀበሌ ተነስቶ ምስራቅ አቅጣጫ በመጓዝ ሂዳሴ መንደርን አቋርጦ አዲስ ዓለም ከተማ የሚገባው ይህ ፕሮጀክት፣ በአጠቃላይ 10.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ቀድሞ የነበረውን የጠጠር መንገድ ወደ አስፋልት ደረጃ የሚያሳድገው ይህ ግንባታ፣ የመንገዱ ስፋት በገጠር 10 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በወረዳ 21.5 ሜትር ሆኖ እየተገነባ ይገኛል። ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሲሆን በአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ... Read More »
9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም(ኢመአ): የመንገድ ልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሳይንሳዊ ምርምርና በቴክኖሎጂ ለማገዝ የተዘጋጀው 9ኛው የመንገድ ጥናትና ሥርፀት ኮንፈረንስ ተካሂዷል። በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን፣ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሂሩት ዮሐንስ እና የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደገብርኤልን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል። ባለፉት ስምንት ዓመታት የተካሄዱት ተከታታይ የምርምር ኮንፈረንሶች በሀገሪቱ የመንገድ ልማት ላይ ውጤታማ ለውጦችን ማምጣት ችለዋል። በአሁኑ 9ኛ ኮንፈረንስም በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን፣ ተያያዥ አውደርዕይም ተካሂዷል።... Read More »
የጣርማበር - መለያያ ሰፌድ ሜዳ የጠጠር መንገድ ጥገና እየተካሄደለት ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21/2018 (ኢመአ)፦ ከጣርማበር መለያያ እስከ ሰፌድ ሜዳ ለሚዘልቀው የጠጠር መንገድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል። ጥገናው የሕዝቡን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል ታስቦ በትኩረት እየተከናወነ ያለ ሥራ ነው። ይህ አጠቃላይ 118 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፣ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት ግንባታው ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሳይጠናቀቅ ተስተጓጉሎ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ግን ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ በሆነው 21.6 ኪሎ ሜትር የመንገዱ ክፍል ላይ ሰፊ የጥገና ሥራ እየተሠራ ይገኛል። እስካሁንም በማሽን የቦይ ማጽዳት፣ የድንጋይ ሙሌት፣ በጭቃ የተበላሹ አካባቢዎችን የማስወገድ እንዲሁም በግሬደር የመንገዱን አካል የማስተካከልና የማጠናከር ሥራዎች ተከናውነዋል። የጥገና... Read More »
የሶዶ መንገድ አውታር አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 1,890 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና አከናወነ፤ አፈጻጸሙም 96.3% ሆኖ ተመዝግቧል
ሶዶ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም(ኢመአ): በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ስር የሚገኘው የሶዶ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት ያቀዳቸውን የፊዚካልና የፋይናንሻል የሥራ ግቦች በስኬት አጠናቀቀ። ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 1.81 ቢሊዮን ብር በጀት መድቦ የነበረ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1.56 ቢሊዮን ብሩን (86.18%) ለተለያዩ የጥገናና መሰረተ ልማት ሥራዎች ማዋል ችሏል። በፊዚካል አፈጻጸም ረገድም ከተቀመጠው 1,963 ኪሎ ሜትር የጥገና ዕቅድ ውስጥ 1,890 ኪሎ ሜትር በማጠናቀቅ 96.3% አፈጻጸም አስመዝግቧል። ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 3,242.5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ሽፋን ያስተዳድረል፡፡ ከዚህም ውስጥ 68 በመቶው (2,196.5 ኪ.ሜ) የአስፋልት ኮንክሪት ሽፋን... Read More »
የቢሻን ጉራቻ - ሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት መገንጠያ መንገድ መልሶ-ግንባታ ፕሮጀክት በትኩረት እየተከናወነ ነው
ሐዋሳ፣ ነሐሴ 12/2018 (ኢ መ አ)፦ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በራስ-ኃይል እየተገነባ የሚገኘው የቢሻን ጉራቻ – ሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት መገንጠያ የመንገድ መልሶ-ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 40 በመቶ መድረሱ ደርሷል። ይህ 1.1 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 26 ሜትር ስፋት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት፤ በሐዋሳ ከተማ መግቢያና መውጫ እንዲሁም በሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ አካባቢ ቀደም ሲል በክረምት ወቅት ይታዩ የነበሩትን የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የውኃ ክምችት እና የመንገድ መበላሸት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ ነው። በአካባቢው ከሐይቁ አቅጣጫ የሚመጣው ውሃ ነባሩን የመንገድ መዋቅር አልፎ መሄድ ባለመቻሉ፣ መንገዱ በውሃና በደለል ተውጦ ለነዋሪዎችና ለተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ችግር መፍጠሩ ይታወሳል። ይህም በከተማዋ የቱሪስት... Read More »
FIND US ON GOOGLE MAP
Call For Conference
