ዜና ዜና

Back

ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኾነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 01/2019 (ኢ መ አ):- ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

ኢንጅነር ሽመልስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (BSc) ያገኙ ሲኾን፣ በተመሳሳይ ተቋም በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኾነው ከመሾማቸው አስቀድሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራ አስኪያጅ እና በኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በቅንነትና በብቃት አገልግለዋል።

ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱ የተቋማችን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሾምዎ እንኳን ደስ ያሎት እያልን የላቀ ስኬትና ውጤት እንዲያስመዘግቡ መላው የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከጎንዎ መሆናችንን እንገልፃለን።