የዋናው ዳይሬክተር መልዕክት የዋናው ዳይሬክተር መልዕክት

አንጋፋው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሰልጣን በትውልዶች ቅብብል አበርክቶቱን እየቸረ ዘመንን የተሻገረ ታሪካዊ ተቋም ነው። ዛሬ ተቋሙ ለደረሰበት ደረጃ ዕነዛ መስራቾቹ በየዘመናቱ አሰተዋጾቸውን እያበረከቱ የመሩት የስራ ሃላፊዎች፤ መላው ታታሪ ሰራተኛ እንዲሁም የባለደርሻ አካላት ተሳትፎ የላቀ ነው። የጎደለውን እያሟሉ ዘመኑ የሚጠይቀውን እየመለሱ፤ ዓለም ከደረሰበት የዘርፉ የልማት ሂደት አኳያ እያነጻጸሩ ኢመባን ወደፊት ለማራመድ የሚያስችል ዘርፈ ብዙ መሰረቶችን ለማሰቀመጥ በተለይም ከባለፉት ሁልት አመታት ወዲህ የተደረጉ ርብርቦች ውጤታማ ለመሆን እየበቁ ነው።

በዓመቱ ውስጥ በተለይም በሁለት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮር የበጀት አመቱን እቅድ ለመፈጸም ጥረት ተደረጓል።

በዚህም መሠረት የመጀመሪያው የተቋሙን የብቃት ሞዴል /Compe­tency Model/ መነሻ በማድረግ የሚተገበረው የኢመባ ተቋማዊና ስትራቴጂያዊ (ቁልፍ) ጉዳዮች ፕሮጀክት ሲሆን ፤ሁለተኛው በሥራ ክፍሎች እለት ተእለት የሚተገበረው የመደበኛ ሥራዎች አፈጻጸም ነው፡፡ በስትራቴጂያ ጉዳዮች በዋናነት በዘርፉም ሆነ በመ/ቤት ደረጃ ለህብረተሰቡ እና ለባለድርሻ አካላት ውጤታማ እና ብቃት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ፤የተቋሙን ሁለንተናዊ የማስፈጸም ብቃት ማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት ተሰረቶበታል፡፡

ይህን ቁልፍ የኢመባ የፍልሰፍና መሰረቶች ሁሉም በተቀራረበ የመረዳት አቅም እንዲገነዘበው የተከናወኑ ውስጣዊና ውጫዊ የምክክር ይስልጠና እና የግምገማ መድረኮች ለተገኙ ተጨባጭ ለውጦች መሰረት እየሆኑ ነው

በአጠቃላይ የመንገድ መሠረተ ልማት ቅድመ ግንባታ ሥራዎችን ግልጽነትንና ጥራት ለማሻሻል እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የሚየበረታቱ እርምጃዎች ተወሰደዋል ባልተለመደ መልኩ የመንግሰትን ውሳኔ ተከትሎ ዲሰትሪክቶችን እና ሴክሽኖችን ከኢመባ ጋር ለማዋሃድ የተሰሩ ስራዎችም ፍሬማ ሆነው ተጠናቀዋል። በእያንዳንዱ የስራ እንቀስቃሴ መሰናከል ይፈጥሩ የነበሩ አበይት ተገዳሮቶችን በመለየት ውል የተገባላቸው ፕሮጀክቶች በወቅቱ የሞቢላይዜሽን ሥራቸውን እንዲያጠናቀቁና ሥራ እንዲጀምሩ እየተደረገ ነው።

በመንገድ ግንባታ ሂደት የሚፈጠሩ የጊዜ ማራዘሚያ እና ተያያዥ ወጪዎችን መቀነስ፣ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በወቅቱ መዝጋት፣ፍትሃዊ የመንገዶች ሥርጭት እና ተደራሽነት እንዲኖር ማስቻል፣ለመንገድ ሀብት ማኔጅመንት ትኩረት በመስጠት የጥገና አቅምን ማሳደግ፣የኮሪዶር ትራንስፖርት ልማትና አለምአቀፋዊ ትስስርን ማጠናከር፣በአገሪቱ እየተከሰተ ያለውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚያስችል ሥራ ማከናወን አሁንም የመልከ ብዙ ባለደርሻ አካላትን ቅንጅት የሚጠይቅ ነው። ኢመባን በተጨባጭ የሚፈታተኑ ተገዳሮቶች አሁንም መልካቸውን እየቀያየሩ ይጻረሩታል። ሀገር ባለመረጋጋት ሂደት ወስጥ ሰትሆን መረጋጋትን እና ፍጹም ሰላምን የሚፈለገው የመንገድ ግንባታ ይቆማል። ፈታኝ የሆነው የወሰን ማስከበር ሂደትም ጊዜን፤ ጉልበትን ወጪን እየደረራረበ መሰኩን ከተገዳሮት አዙሪት ውስጥ ይከተዋል። ስልጡን የሰው ሃይል እና የተቋራጮች ብሎም የአማካሪዎች የተለያዩ ውስንነቶች ተጨማሪ ፈተናዎች ናቸው እነዚህ ተግዳሮቶች በከፍተኛ ደረጃ እየደገ ከሄደው የህዝባችን የመንገድ መሰረተ ልማት ፋላጎት ጋር ቢያንስ ተቀራረበው እንዲጓዙ ያላሰለሰ ጥረቶችን ይጠይቃል። ወቅታዊው የኮሮና ወረርሺኝ ለዘርፉ መደናገጥ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ነው። የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ እየተወሰዱ ያሉ የመፈትሄና የጥንቃቄ እርምጃዎችን አጣጥሞ ለመምራት የተደረገው ጥረት የጎላ ቢሆንም ቀጣይ ክትትልና ድጋፍን የሚሻ ነው።

ቀጣዩ ምዕራፍ ለሀገራችን ብሩህ ነው ተቋማችን በዚህ የታሪክ ሂደት ውስጥ ይብልጥ ሚናወን የሚወጣብት ስራ አበርክቶ ለማለፍ ደፋ ቀና ማለቱን ቀጥሏል። ኢመባ ይብልጥ ሰርቶ የሚያሰራ አደረጃጀትን እንዲከተል እየተደረገ ነው ለመላው ሰራተኛ ጥቅማ ጥቅምን ከሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ ለመጓዝ የሚያስችሉ ውሳኔዎችም ተወሰነዋል። አመታዊ የመፈጸም አቅሙ እና ሰርቶ የማሰራት ብቃቱ እየጎለበተ መምጣቱን ተከትሎ ከመንግስት የሚመደቡ በጀቶችም እየገዘፉ መተዋል መላው ህዝብ ተቋማችንን እየተመለከተ ነው። ይህን ሀገራዊ አደራና ሃላፊነት በላቀ ብቃትና ተነሳሽነት ለመፈጻም መላው አመራር እንዲሁም ሰራተኛ የሚታዩ ወስንንቶችን በመሻገር ለላቃ ውጤታማነት ይብልጥ እንደትነሳሱ የአክብሮት ጥሪዬ ነው።